የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ Aug 22, 2020
|
HEBREZEMA.INFO INDEPENDENT NEWS & MEDIA DESIGNED BY ZEWDU TEKLU © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
|
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር በወታደራዊ
አመራርነት ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ፡፡
ሉዓላዊንትና የህዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ወታደራዊ አመራሮች በዕውቀት ላይ ተመስርተው ሀገርን እና
ህዝብን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል ጠንካራ ሀይል መገንባት
መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የኮሌጁ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጀነራል ዳኛቸው ይትባረክ በበኩላቸው፥ ዛሬ በከፍተኛ ስልታዊ አመራር 90
ስልጣኞች መመረቃቸውን ገልፀው ÷ 18ቱ ከአምስት የጎረቤት ሀገር የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
በስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ሀሰን ኢብራሂምን ጨምሮ
ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡