Home    News     States     Investment     Tourism     Sport    Entertainm.    Radio & Tv     About us     Contact      Links     Archives
admin@hebrezema.info
1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
የመለስ መታሰቢያ ቀን ይከበራል
July 20 2013
የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ አንደኛ አመት መታሰቢያ ነሐሴ
14/2004 ዓ.ም “መለስ ቃልህ ይከበራል” ወደላቀ ደረጃ
ለማድረስም ቃላችንን አናድሳለን በሚል መሪ ቃል
ይከበራል፡፡

የመለስ ፋውንዴሽን ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ካሣ
ተክለብርሃን ነሐሴ 14 ቀን 2005 ዓ.ም አዲስ በሚመሰረተው
የመለስ ፋውንዴሽን ሙዚየምና ፓርክ የተለያዩ የህብረተሰብ
ክፍሎች ተወካዮችና የውጭ ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት
የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል ብለዋል፡፡

አቶ ካሣ እንዳሉት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በኢትዮጵያ
ሁሉም አካባቢዎች በመለስ ስም በተሰየሙ አካባቢዎች የችግኝ
ተከላ ሥራ እንደሚከናወን የገለጹ ሲሆን ነሐሴ 13 ቀን 2005
ዓ.ም ደግሞ በየተቋማቱ በመሰባሰብ በሻማ ማብራት ሥነ-
ሥርዓት ታስቦ እንደሚውል ገልጸዋል፡፡

የመለስ ፋውንዴሽን ቦርድ ሰበሳቢ ወ/ሮ አዜብ መስፍን
በበኩላቸው የመለስ ፋውንዴሽን የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ
መሆኑን በመግለጽ ታላቁ መሪ መለስ በህይወት በኖሩባቸው
ወቅት የጻፏቸውን የጽሁፍ ሥራዎችና ሳይታተሙ ዋናውን ኮፒ
ለህብረተሰቡ ይፋ የሚደረግበትን መንገድ በማመቻቸት መረጃ
ለሚፈልጉ ሁሉ እንደማመሳከሪያነት ያገለግላል ብለዋል፡  

ወ/ሮ አዜብ በመቀጠልም መለስን በህብረተሰቡ ውስጥ ይበልጥ
ለማስተዋወቅ በመጽሃፍ፣ በዶክመንተሪ እና መሰል መንገዶች
እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በመለስ ፋውንዴሽን ላይ ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ
ለመሳተፍ የሚፈልጉ እንዳሉ በማሰብም በ ኤስ ኤም ኤስ
መልእክት ከ2 ብር ጀምሮ እስከ 1መቶ ብር ድረስ እንዲሳተፍ
እንዲሁም ከዚህ በላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ደግሞ በአዲስ
አበባና ክልል ከተሞች የባንክ አካውንት በመክፈት
እንዲሳተፉ ለማድረግ ታስቧል ይህም በቅርቡ ይፋ ይደረጋል
ነው ያሉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፡፡
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ “መለስ ቃልህ ይክበራል
የጀመርከወ ይፈጸማል” በሚል መሪቃል ድህነትን ለማጥፋት፣ አረንጓዴ ልማትን ለማብሰር፣ መልካም አስተዳደርን
ለማስፈን ያሳየውን ቁርጠኝነትም በመለስ ፋውንዲሽን ሥም አመስግነዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ጌቱ ላቀው