Home    News     States     Investment     Tourism     Sport    Entertainm.    Radio & Tv     About us     Contact      Links     Archives
admin@hebrezema.info
1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
በዚህ ረገድ በየትኛውም መንገድ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ጥቅምና ጥቅምን ብቻ መሰረት ያደረገ ይሆናል።

ግብፅ አሁን ያለመረጋጋት ውስጥ ገብታለች ፤ የሃገሪቱ ጦር ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ሙርሲን ከሃላፊነት በማንሳት በምትካቸው
አዲሊ ማንሱርን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ሹሟል።

አምባሳደር ዲና እንደሚሉት ይሄ የግብፅ ያለመረጋጋት በተዘዋዋሪ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠናም ሊተርፍ ይችላል።

ኢትዮጵያም በማንኛውም ሃገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የሌላት መሆኑን የገለፁት አምባሳደሩ ፥ በግብፅ
የሚመሰረተው መንግስት ለአካባቢው ሰላም መስፈን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አብሮ የሚሰራ መንግስት እንዲሆን የኢትየጵያ
ፅኑ አቋም መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ የሚመጣው መንግስት የውጭ ፖሊሲ ምን ሊሆን እንደሚችል ማጤን እንደሚጠይቅ ጠቅሰው ፥ ከዚህ መነሻነት የሚመጣውን
የሃይል አሰላለፍ ፣ ፍላጎትና የፖለቲካ ጥንክር እያደር ማየቱ ይበጃል ባይ ናቸው።

ያም ሆነ ይህ ግን አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ኢትዮጵያን በተመለከተ ሊከተለው የሚችለው ፖሊሲ በቅርብ ጊዜያት የሚታይ
እንደሆነ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

ለምንም ነገር ክፍት ሊሆን በሚችል ያልተረጋጋ አካባቢ መኖር አስቸጋሪነቱን ያየነው በመሆኑ ሌላ ያልተረጋጋ አካባቢ
እንዲፈጠር የኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳልሆነም አምባሳደር ዲና አስረድተዋል።
በታደሰ ብዙአለም
ኢትዮጵያ የግብፅን ሰላምና መረጋጋት
አጥብቃ ትሻለች -
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
julay 4 20013
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ
የግብፅን ሰላምና መረጋጋት አጥብቃ እንደምትሻ የውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ
ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ኢትዮጵያ
ከሃገራት ጋር በሚኖራት ግንኙነት ላይ አትኩሮ ግብፅን
በተመለከተ ፤
ከግብጽ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ተወደደም
ተጠላ የአባይ ጉዳይ የግንኙነቱ ማዕከል መሆኑ አይቀርም ፤
በዚህ ረገድ የምንከተለው ፖሊሰ የአባይ ጉዳይ ጥቅሞችን
ለማጣጣም መርህ ፣ ለሰላምና ለድርድር የልማት
እንቅስቃሴያችንን በማይጎዳ መልኩ እንዲፈታ ማድረግ
ይሆናል።

ከዚህ ጎን ለጎን በዚህ ጉዳይ ሊታዩ ለሚችሉ ስጋቶች ያለንን
ተጋላጭነት መቀነስ የሚያስችል ፖሊሲ ሊኖረን ይገባል የሚል
ዝርዝር አለው።