Home    News     States     Investment     Tourism     Sport    Entertainm.    Radio & Tv     About us     Contact      Links     Archives
admin@hebrezema.info
1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.

በሀይማኖት ሽፋን እያቆጠቆጠ ያለው የአክራሪነትና የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በጉባኤተኞቹ የተወገዘ ሲሆን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ
የአክራሪ ሃይሎች የጥፋት ድርጊት መሳሪያ የሆኑ ወገኖች ከስህተታቸው ታርመው ለሰላምና ልማት መረጋገጥ በፅናት እንዲቆሙም
ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በጉባኤው ለመላው ህብረተሰብ ወጣቶችና ሴቶችን በመልካም ስነምግባር በማነፅና በሀገር ፍቅር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አስፈላጊውን
ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአደራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሪፖርተር ናትናኤል ፀጋዬ
የሰላም እሴት ማጎልበቻ አገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቀቀ
August 28 2013
በኢትዮጵያ ያለው የሀይማኖቶች መቻቻልና በሰላም አብሮ
የመኖር ባህል ለማጎልበትና ለማስቀጠል እንደሚሰሩ የአገር
አቀፍ ጉባኤ ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫ  
አረጋግጡ፡፡

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት
ጉባኤ ትብብር ከነሀሴ 21­­­ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ
የነበረው የሰላም እሴት ማጎልበቻ አገር አቀፍ ጉባኤ ባለ 7
ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ዛሬ ተጠናቋል፡፡

የአቋም መግለጫው የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ በተጠናከረ
ሁኔታ ለማራመድ በቀጣይ የትኩረት ማእከል አድርገን በጋራ
ልንረባረብባቸው በሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት
አድርጎ የወጣ እንደሆነ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
ገልጿል፡፡

ጉባኤው ባወጣው የአቋም መግለጫ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ
ረጅምና ጥልቅ የሀይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር ባህልና
ታሪክ ያላት ሀገር በመሆኗ ይህንን ለመስቀጠል የጉባኤው
ተሳታፊ ግንባር ቀደም ሆነው ለመስራት፣ ህገመንግስታዊ
ግንዛቤና ንቃተ ህግ እንዲዳብርና ለህግ የበላይነትም
የማክበርና የማስከበር የዜግነት ድርሻ ለመወጣት
በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀሱ ቃል ገብተዋል፡፡