በጀርመን የትብብር ድጋፍ ተጠየቀ

Sunday, 6 February 2022

በጀርመን የኢትዮጵያ ፌ.ዴ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሣደር ክብርት ሙሉ ሠሎሞን አዲሡ የጀርመን መንግሥት ፣ በልዩ ልዩ የትብብር መሥኮች ከወትሮው በበለጠ ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቁ። ክብርት አምባሠደሯ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና የሣህል ዳሬክተር ከሆኑት አምባሳደር ሮበርት ዶልገር ጋር በ02.02.2022 በአካል በመገኘት ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በማሥረዳት፣ TPLF በኢትዮጵያ ክልሎች በአማራና በአፋር የሚያደረገውን ትንኮሣና የንፁሀንና ሠላማዊ ሠዎች ጭፍጨፋ ፣ እንዲሁም መተላለፌያ ኮሪደሮችን እየዘጋ ለትግራይ ህዝብ ሠብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ ማገዱን በይፋ እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።


አሸባሪውን TPLF በወረራ ከገባበት የአማራና የአፋር ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት ካሥወጣው በኃላ በሠሜኑ ክፍል አንጻራዊ ሠላም መኖሩን ገልጸው፣ ''በሌሎች ክልሎች እና በአዲስ አበባም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሠላም የለም፣ ከሀገር ውጡ '' በማለት በሀገራችን ላይ የተሠነዘረው የሀሠት ዜና ፣ አደገኛና አፍራሽ የወሬ ዘመቻ በመላው ሕዝባችን ርብርብና አንድነት መክሸፋ ፣ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ሠላም ያለውን ፋይዳ እንዲረዱ ፣ ጀርመን በአውሮፓ ህብረትም ውሥጥም ባላት የተጽኖ ፈጣሪነት ሚናዋ፣ TPLF ላደናቀፈው የሠብአዊ አርዳታ ፍሠት ፣ የኢትዮጵያን መንግስት ያለአግባብ መውቀሥና መጫን መቆም እንዳለበትና ተገቢው ድጋፍ ለኢትዮጵያ አንዲሠጥ ጠይቀዋል። በበርካታ የጋራ ጉዳዮች ላይ በጥሩ መግባባትም ተወያይተዋል ።


አምባሣደር ሙሉ ለሁሉም የሀገራችን ወሣኝ ጉዳዮችና በወሣኝ ወቅት ጭምር ላለፋት ሶስት ዓመታት የጀርመን መንግሥት ላደረገው ድጋፍ እና በቅርቡም ላደረገው የ80.6ሚሊዮን ዩሮ ( ሠማንያ ሚሊዮን ስደስት መቶ ሽህ ይሮ ) አና ልዩ ልዩ ድጋፎች አመሥግነዋል።