በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ዳያሥፖራው ውይይት አደረጉ

Tuesday February 08, 2022

በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ዳያሥፖራው ውይይት አደረጉ ።


በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአሁኑ ወቅት ከሚሸፍናቸው ሀገሮች ፣ ማለትም በጀርመን፣ በቼክ ሪፐብሊክ፣ በፖላንድ ሪፐብሊክ ፣ በስሎቫክ ሪፐብሊክ፣ በዮክሬይን በስዊድን ፣ በኖርወይ ፣ በዴንማርክ ፣ እና በፊንላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ - ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይና በኤምባሲው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥር 22 ቀን 2014 ዓ.ም 'በዙም' ውይይት ተድርጓል ።


በጀርመን የኢትዮጵያ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ሙሉ ሰሎሞን "በአንድነት ስንቆም ተራራው በራሡ ይፈርሳል!" በሚል ሀሳብ በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ ማብራሪያ በመስጠት ቀጣይነት ባለዉ መልኩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ - ኢትዮጵያውያን እነደሁልጊዜውም በህብረት በጽናት በመቆም ማንኛውንም ተራራ የሆነ ችግር እንደሚያፈርሡ እምነታቸው መሆኑን ገልጰው፣ የዳያሥፖራውን ያላሠለሠ ድጋፍ በማመሥገን መልእክት አስተላልፈዋል ።


የህዳሴ ግድባችንም ሀይል ማመንጨት በመጀመሩ፣ ደሥታቸውን ገልጸው፣ የሁሉም ድጋፍ ፣ ርብርብ እና አንድነት ውጤት በመሆኑ አመሥግነዋል። ለዘንድሮው የህዳሤ ግድብ ሙሊትም የተጀመረው ድጋፍ እንዲቀጥል፣ ለተጉዱ ውገኖቻችን ፣ በአማራና በፋር ክልል የፈረሡ ጤና ጣቢያዎች፣ ት/ቤቶች ፣መሠረተ ልመቶችን ወ.ዘ.ተ.በጋራ ባሉን ግንኙነቶች በመጠቀም በመገንባት ደጋፋችንን በማጠናከር ፣ የተለመደ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅነታችንን አናረጋግጥ ብለዋል።


በቅርቡ ወደ ኢምባሲው የመጡት ምክትል ሚሲዮን መሪ፣ አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ ከተሣታፈው ጋር የተዋወቁ ሲሆን፣ ከተዘጉ ሚሲዮኖች የተዛወሩና ሠራተኛ አስኪመደብ የዘገዩ የቆንሥላ ግልጋሎቶች ባለው የሠው ሀይል በመረባረብ በቅርቡ እንደሚጠናቀቁ ትልቅ ተስፋ ሠጥተው የዳያሥፖራውን እገዛ እና ትብብር አስፈላጊነት ገልጸዋል።


በመድረኩ ላይ በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ እና በሚሲዮኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተሣታፊዎቹ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል ። በመጨረሻም ለዳያሥፖራው ቀጣይነት ያለው ጥቅምና እውቅና የሚሠጥ ሁሉን ማህበራት ያቀፈ ከሁለት ዓመት በፊት በአንዳንድ ከተሞች ተጀምሮ በኮሮና ስለተቋረጠው የደዳያሥፓራ ካውንሥል የማቋቋም ጉዳይ፣ በየከተማው እና በየሀገሩ እንዲቋቋም፣ ውይይት ተደርጓል። ስለ ዝርዝር ሁኔታው ናሙና ሠነድ እንዲላክ እና ሁሉም እነደየሀገሩ ሁኔታ መደራጀት እንደሚጀምር ግንዛቤ ተወሰዷልል።