ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ተወያዩ

Tuesday February 08, 2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህርስቶር ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ አጋርነት ትገነዘባለች ብለዋል።