ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ተጠናቀቀ

Friday February 11, 2022

ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ዛሬ መጠናቀቁን የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አስታወቀ። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው÷ ሥልጠናው ከፍተኛ አመራሩ የተጣለበትን ሃላፊነት በብቃት መወጣት ይችል ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የሥራ አፈጻጸም፣ የሥነ ምግባርና የአገልጋይነት አቅሙን ለማጎልበት የተዘጋጀ ነው።


ከፍተኛ አመራሮቹ በሥልጠናው ህዝቡ የጣለባቸውን ሀላፊነት በከፍተኛ ትጋትና ቁርጠኝነት እንደሚወጡ ገልጸው÷ በየተቋሞቻቸው የአገልጋይነት አመራርን ተግባራዊ በማድረግና የህዝቡን የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመመለስ የዜጎቻችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡ ተመሳሳይ የአመራር የአቅም ግንባታ መድረኮች በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ መዋቅሮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ ብሏል ጽ/ቤቱ ።