መከላከያ ሰራዊት ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጠረ

November 27 2021

(ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መላውን የጸጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የህልውና ዘመቻውን ከዳር ለማድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን አስታወቀ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሓት ነጻ ያወጣ ሲሆን ወደፊት በመገሥገሥ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ እና ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው ብሏል። በአፋር ክልል፣ በጭፍራ ግንባርም ጪፍቱን፣ የጭፍራ ከተማንና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገሥገሦ ላይ ነው።