ርዕሰ መስተዳድሮቹ የሁለቱን ክልሎች የጋራ የሠላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግንባታ አስጀመሩ

Friday February 11, 2022

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሁለቱን ክልሎች የጋራ የሠላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ግንባታ በአሶሳ ከተማ አስጀመሩ።


የጽሕፈት ቤት ግንባታው በ30 ሚሊዮን ብር እንደሚከናወን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡