በመዲናዋ አምስት የቀበሌ መታወቂያና 25 የባንክ ደብተሮች የተገኘበት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

September 4,3031

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩና ማንኛውንም አገልግሎት ሲፈልጉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) ወስኗል።


ጨፌው 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል። በጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እውቅና መስጠት የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ፀድቋል።


አፈ ጉባኤዋ በማብራሪያቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የአገር ሉዓላዊነት የመድፈር ወንጀል ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነትና መስዋእትነት ጭምር መቀልበሱን ጠቅሰዋል።


“በዚህም ለአገር መከላከያ ሰራዊት እውቅና መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል። የክልሉን የ2013 በጀት አመት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ለጨፌው ያቀረቡት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በበጀት ዓመቱ በክልሉ የተለያዩ ችግሮች ያጋጠሙ ቢሆንም የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል” ብለዋል።


የህግ የበላይነትን በማስከበር የተቃጡ ሴራዎችን የማክሸፍ እንዲሁም የመሬት ወረራን እና ህገ ወጥ ስራዎችን የመከላከል ስራ በስፋት መከናወኑን አብራርተዋል። በክልሉ በ31 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 11 ሺህ የልማት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሰዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማግኘታቸውን፣ የመንገድ እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች እንዲሁም የትምህርትና የጤና መሰረተ ልማቶች መከናወናቸውንም እንዲሁ።


በተከናወነው ልማት 62 የጤና ተቋማት ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ መግባታቸውንና 67 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ እንደተጠናቀቀም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፤ 86 ቢሊዮን ብር ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ክልሉ ገብተው ማልማት መጀመራቸውን ተናግረዋል። በ18 ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ አረንጓዴ ስፍራ የማዘጋጀት ስራ እንደተሰራና በቱሪዝም ዘርፉ 45 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰዋል።


የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራን በማጠናከር ኦቢኤን በ18 ቋንቋዎች የሚዲያ ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል። በአጠቃላይ 36 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መደበኛ እና የመዘጋጃ ቤት ገቢ እንደተገኘም ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ የ2014 ዓ.ም 13 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ መታቀዱንም ተናግረዋል።