የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ያስቀመጡትን ግብ ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግበዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ

Thursday, 6 January 2022

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በየዘርፋቸው ለመምታት ያስቀመጡትን ግብ ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ። የሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነው ጉባ እየተካሄደ ይገኛል። በግምገማውም የተገኙ ውጤቶችን ማጽናት እና በላቀ ሁኔታ ማስቀጠል የሚቻልበትን እንዲሁም ካጋጠሙ ተግዳሮቶች እድሎችን መፍጠር የሚቻልበትን አቅጣጫ ማስቀመጡንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት ፅሁፍ አመልክተዋል።