አቶ ደመቀ መኮንን በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ጉብኝት አደረጉ

November 11, 2022

አንዳንድ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት’ ሰብአዊ ድጋፍ እንሰጣለን’ በሚል የሚፈጽሙትን አገር አፍራሽ ተልዕኮ በመቃኘት መንግስት አብሮ የመስራት እንቀስቃሴውን እንደሚቃኘውና አንዳንዶቹንም ከአገር የማስወጣት ስራ እንደሚሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።


አምባሳደር ሬድዋን መንግስት የወሰነውን ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተናጠል ተኩስ አቁምና ተያያዥ ወቅታዊ የአገርና አለም አቀፍ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸው መንግስት ሰብአዊነትን ያስቀደመ፣ የሚደርሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሉአላዊነት ላይ የተደቀኑ ችግሮችን ምክንያት በማድረግ የተናጠል ተኩስ አቁም ማድረጉን አስታውሰዋል።


“ውሳኔው በአለም አቀፍ ደረጃ የሚነሱ ግፊቶችን ምላሽ የሰጠና ለኢትዮጵያ ደህነነትና ሰላም ተጨንቀው ለነበሩት ደግሞ እፎይታን የሚሰጥ ነበር ተብሎ ይታመናል” ብለዋል። “ከውሳኔው በኋላ አፍራሽ የነበሩ ዝንባሌችን መንግስት ለመታዘብ ችሏል” ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ መንግስት ተኩስ አቁሙን ወስኖ ሲወጣ ሲቃጡ የነበሩ የተኩስ አቁም የጥሰት ድርጊቶችን ግን ለማውገዝ በአለም አቀፍ ደረጃ የታየው ተነሳሽነት አናሳ መሆኑን አብራርተዋል። አንዳንድ አካላትም አወንታዊ ውሳኔውን ከማድነቅ፣ ከመደገፍና የጎደለውን ከመሙላትና ከማሳሰብ ይልቅ አፍራሽንና አሉታዊ ምክንያቶችን በመደርደር የውሳኔውን አናሳነት ለማጉላት መንቀሳቀሳቸውን ገልጸዋል።


“በጦር ወንጀልነት አለም የፈረጃቸውን ህጻናትን በጦርነት የማሰለፍ የመመልመል እንቅስቃሴ እየታየ አለም አቀፍ ሚዲያና አንዳንድ አካላት ሊያወግዙ ሲገባ ነገሩን እንዳላዩና አንዳልሰሙ ሆነዋል” ብለዋል።


የምዕራባውን የሚዲያ ተቋማት ይህንን ድርጊት እንደ ወታደራዊ ሚዛን በአወንታነት ለመዘገብ ያሳዩት ድርጊትም ጎላ ያለ ትዝብት ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች የሚያደርገውን ትንኮሳ ለመኮነን፣ ለማውገዝ፣ ለማጋለጥና ለመኮነን የሚደረገው ሙከራ አነስተኛ ሆኖ ታይቷል ሲሉ አብራርተዋል።


“መንግስት የተኩስ አቁሙን ያደረገው ለህዝቡ እፎይታ፣ ለሰላሙም እድል ለመስጠት እንጂ የግጭቱን ቀጠናና ስፍራ ለመቀየር አልነበረም፣ ሆኖም የተኩስ ማቆሙ ሲጣስ መቆም አለበት ብሎ የሚኮንን አካል ብዙ አለመሆኑ መንግስት ግጭቱ መቆም አይፈለግም ወይ የሚለውን ጥያቄ እንዲያነሳ አድርጎታል” ሲሉ ገልጸዋል።


“መንግስት በስፍራው የሰብአዊ ድጋፍ የሚደረግባቸውን ምቹ ሁኔታዎች ፈጥሮ እያለ ክሶች ሲቀርቡ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ድጋፍ የማቅረብ አለመሆኑ ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው” ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ሰብአዊ ድጋፍ እናስተባብራልን የሚሉ አንዳንድ አካላት ከእርዳታ አቅርቦት ጋር በማያያዝ አፍራሽ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። “እዚህ ከተመደቡት የእርዳታ አስተባባሪዎች ይልቅ ከርቀት ላይ ሆነው ከእርዳታ ይልቅ የፕሮፓጋንዳ ስራና መንግስትን የማዋከብ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል” ብለዋል።


“በዚህም መንግስት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል” ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ ጉዳዩ የሚቀጥል ከሆነ አገር የማዳን ሃላፊነቱን ስለሚወጣ ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ የመስራት እንቀስቃሴውን እንደሚቃኘውና አንዳንዶቹንም ከአገር የማስወጣት ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።


የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ይሁን ማንኛውም እርዳታ አቅራቢ አካል ሰብአዊ ድጋፍ ላይ ብቻ ታጥሮ መንቀሳቀስ እንደሚገባው አሳስበዋል።


በድንበርና በታላቁ ህዳሴ ግድብና በአገሪቱ ያሉ ችግሮችን በመመርኮዝ የጥፋት ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ጠቁመው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በህዳሴ ግድቡና በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሳየውን አንድነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ህብረተሰቡ በአንድነት፣ በመደማመጥ፣ በመቻቻል፣ በመተጋገዝና በሰከነ ሁኔታ ችግሩን ማለፍ እንደሚገባው አመልክተው፤ የፌዴራል መንግስቱ የሚሰጠውን አቅጣጫ በመከተል እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።