አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆናቸውን ገለጹ

November 11, 2022

በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። በክልሉ 70 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ዕርዳታው ከመቼውም ጊዜ በላይ እየደረሰ የጠቆሙት ሚኒስትሩ ዕርዳታውን በሌሎች ቀሪ አካባቢዎች ለማዳረስ በ35 ተሽከርካሪዎች ምግብ እና በ3 ተሽከርካሪዎች መድኃኒት ተጭኖ ሽሬ ገብቷል ብለዋል።


አምባሳደር ሬድዋን በቲውተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ ወደ ክልሉ በረራ መፈቀዱንና የሰብአዊ ዕርዳታን በተመለከተ ምንም ዓይነት መሰናክል እንደማይፈጠር አመልክተዋል። አንዳንድ አካላት የአፍሪካዊያን ዕውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት ደስተኛ እንዳልሆኑ ጠቁመው ይህንን መልካም መንፈስ ለማወክ ሲጥሩ ይታያሉ ሲሉም ገልጸዋል።

waltainfo.com