የኦሮሚያ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የተለያዩ የክልሉ አመራሮች ልኡክ ጅግጅጋ የገባ ሲሆን ፥ ልኡካን ቡድኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና የተለያዩ የክልሉ የመንግስት የስራ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
አቶ ሽመልስ አብዲሳና ልኡካቸው ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ጋር በመወያየት በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ የሚሆን የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡