1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
8ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ
June 12, 2018
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) 8ኛ ድርጅታዊ
ኮንፍረንስ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

ከእሁድ ሰኔ 3 2010 ዓ.ም አንስቶ ለሶስት ቀናት የተካሄደው ውይይቱ በተለያዩ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ
ሲመክር ቆይቶ ነው ዛሬ የተጠናቀቀው።

የኮንፍረስኑ ማጠቃለያ ላይም የኢህአዴግ እና የኦህዴድ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኦህዴድ ምክትል
ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ ከድርጅቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም ስለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ማብራሪያ
ሰጥተዋል።

የኦህዴድ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ኮንፍረንሱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥
በኮንፍረንሱ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች መለየታቸውን እና ጉድለቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም
የህዝቡን ተጠቃሚነት በሚረጋገጥበት መልኩ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

ከጥቅል ተሃድሶ ወዲህ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም ሰፋፊ ጉድለቶች እየታዩ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች፥ ለተፈጠሩ ጉድለቶች
ምክንያቶችን በመለየት በቀጣይ ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት መልኩ በቁርጠኝነት ለመስራት ከስምምነት ላይ
መደረሱንም አንስተዋል።

ጠንካራ የሆነ አመራር ባለበት ታላላቅ ስኬቶች መመዝገባቸውን ያስታወቁት ወይዘሮ አዳነች፥ ደካማ አመራር ባለባቸው
አካባቢዎች ደግሞ የህዝብን ጥያቄ ከመቅረፍ ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን እና ይህንን ችግር ለመቅረፍን ከላይ እስከ
ታች ማስተካከያ መደረጉንም አስታውቀዋል።

ወይዘሮ አዳነች አክለውም በመድረኩ አሁንም ከወሰን ጋር ተያይዞ ችግርች እንዳሉ መነሳቱን ገልፀው፤ ችግሩ በህዝብ
መሃል ሳይሆን በግለሰቦች የሚፈጠር መሆኑን እና ይህንን ለማስቆመም በየክልሎቹ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑ
በመድረኩ ተብራርቷል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ማግኘት የሚገባው ጥቅም ጉዳይ ለምን ዘገየ በሚለው ላይም፤ በጉዳዩ ላይ እየተሰራ
መሆኑን እና በክልሉ ውስጥ በሚገኙ እስከ ታች ምክር ቤቶች ድረስ ሰነዱ ለውይይት መላኩም በመድረኩ መነሳቱን
አስታውቀዋል።

አፋን ኦሮሞን የፌደራል የስሯ ቋንቋ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን እንስቅሴ አስመልክቶ ለተነሳው ጥያቄም ድርጅቱ
በዚህ ላይ አቋም ይዞ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ኮንፍረንሱ በመጨረሻም ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በአቋም መግለጫውም የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች የድርጅቱን የውስጠ ጥንካሬ የአመለካከት እና የአስተሳሰብ አንድነትን
ለማጠናከር አካባቢያዊነት፣ ጎሰኝነትና ጎጠኝነትን፤ በሀይማኖትና በእንመት መለያየትን በፅኑ እንደሚዋጉ አስታውቀዋል።

ኦህዴድ ኪራይ ሰብሳቢነትን ከምንጩ ለማድረቅ እንዲሁም በቁጥር እና በባህሪያቸው የተለዩ የልማት እና የመልካም
አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ኦህዴድ ባስቀመጠው አቅጣጫን መሰረት እንደሚረሱም ገልፀዋል።

የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ የአብሮነትና ሀገራዊ ስሜት አንዲያድግና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለጋራ ልማትና ሀገራዊ አንድነት
እንዲያገለግል በማድረግ እንዲሁም በፖለቲካው ረገድ መመዝገብ የጀመሩ ድሎችን ወደ ተሻለ ደረጃ ከማሸጋገር ጎን
ለጎን የኢኮኖሚው ሂደትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚታገሉም አስታውቀዋል።

የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በአቋም መግለጫቸው አክለውም በድርጅቱ ውሳኔ እና አቅጣጫዎች መሰረት በመንቀሳቀስ
የውስጠ ድርጅት ክፍተቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

እየመጣ ያለው ለውጥ በሚፈለገው መጠንና ደረጃ ለመተግበር የሚፈለገውን ብቃት እና ክህሎት በማዳበር ብቃት ያለው
አመራር ለመስጠት የሚያስችል ቁመና መላበስ እና የህዝብን የእርካታ መጠን ማሳደግ ግዴታ በመሆኑ ይህንን
እንደሚያረጋግጡ አስታውቀዋል።

አሁን ባለው ወሳኝ የትግል ምእራፍ ላይ የተላለፉ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን በመተግበር የሀገሪቱን እና የክልሉን የህዳሴ ጉዞ
ላንድም ሰከንድ ሳይደናቀፍ በስኬት እንዲጓዝ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በአቋም
መግለጫቸው አስታውቀዋል።
admin@hebrezema.info
1