1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
admin@hebrezema.info
ደኢህዴን በጥልቅ ተሀድሶ ግምገማው 910 አመራሮች ከሀላፊነት መነሳታቸውን
አስታወቀ
January 22, 2017
በመጀመሪያው የጥልቅ ተሀድሶ ግምገማ 910 አመራሮች ከሀላፊነት መነሳታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
(ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

ከሃላፊነታው ከተነሱት አመራሮች መካከልም 265 የሚሆኑት በህዝብ ትችት መነሳታቸው ነው የተነገረው፡፡

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፥ የመጀመሪያው ምዕራፍ የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ መጠናቀቅን
አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የተግባር አፈጻጸም ችግሮችን በመለየት ሁሉም አመራር ለለውጥ የተነሳሳበት ነበር ብለዋል፡፡

በጥልቅ ተሀድሶው 10 ሺህ 573 አመራሮች መገምገማቸውንም ነው አቶ ተስፋዬ የተናገሩት፡፡

ምሁራንን ጨምሮ ብቃት ያላቸው 1 ሺህ 545 አመራሮች ወደ ሀላፊነት መምጣታቸውን ጠቅሰው፥ 612 ነባር አመራሮች ደግሞ
ተሸጋሽገዋል ተናግረዋል፡፡

ያልተገባ ጥቅም ላይ ሲውል ከነበረ 6 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥም 3 ሺህ ሄክታር መሬት የተመለሰ ሲሆን፥ ከተመዘበረ 32 ሚሊየን ብር
ውስጥ ደግሞ 11 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ወደ መንግስት ካዝና ተመልሷል ነው ያሉት፡፡

በክልሉ የተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የጥልቅ ተሀድሶ መላውን ህዝብ ያሳተፈ በመሆኑ ውጤታማ እንደነበር አቶ ተስፋዬ አንስተዋል፡፡


ሀላፊው እንዳሉትም በችግር ውስጥ የተዘፈቁ 87 አመራሮች ህጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን፥ ከነገ ጀምሮ ሁለተኛው ምዕራፍ የጥልቅ
ተሀድሶ በተግባር ላይ አተኩሮ ይጀምራል፡፡
1