1
States
Investment
Tourism
Sport
Entertainm.
Radio & Tv  
About us
Contact  
Links
Archives  
ከ30 በላይ ወለሎች ያሉት ባለሰባት ኮከብ ሆቴል ሊገነባ ነው
10 February 2021
    Home             News          States         Investment   Tourism         Sport          Entertainm.      Radio & Tv     About us        Contact      Links                  Archives
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
1
ታምሩ ጽጌ
ጄኤች ሲሜክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በመሀል ካዛንችስ ከ12 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው
‹‹ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል›› ስያሜን በአዲስ ብራንድ በመተካት፣ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ከ30 በላይ ወለሎች
ያሉት ባለሰባት ክከብ ሆቴል ሊገነባ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

በአቶ ስማቸው ከበደ የሚመራው ጄኤች ሲሜክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማክሰኞ የካቲት 2
ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ኢንቨስትመንት የበለጠ
በማስፋፋትና በማዘመን ድርጅታዊ መዋቅሩንና ዓለም አቀፍ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ለማሳደግ ወስኗል፡፡

ኢንቨስትመንቱንም በዘመናዊ አሠራርና በቴክኖሎጂ የተመራ በማድረግ፣ ወቅቱ በሚጠይቀው አዲስ አደረጃጀት
መንቀሳቀስ በማስፈለጉና ውሳኔ ላይ በመደረሱ፣ በቀጣይ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅና በአፍሪካ ደረጃ
ተወዳዳሪ የሚሆን ከ30 በላይ ወለሎች ያሉት ባለሰባት ኮከብ ሆቴል ለመገንባት የዲዛይን ቀረፃ በአገር ውስጥና በውጭ
አገር ባለሙያዎች አሠርቶና አስገምግሞ ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴልን በሥራ አስኪያጅነት እየመሩት የሚገኙት አቶ ወገኔ ማትያስ እንደገለጹት፣ ማኅበሩ
የተሰማራበት ኢንቨስትመንትን በማጠናከርና አዳዲስ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ቆርጦ መነሳቱን ጠቁመው
በቅርቡ የሚጀመረው የሌግዥሪ ሆቴል ግንባታ የሚያከናውነው ኢንተርኮንቲኔንታል የሚለውን ስያሜ በመተካት፣ በራሱና
ዓለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው ብራንድ ሆቴሎች ስያሜ ጋር በማጣመር አዲስ ስያሜ እንደሚመጣም አብራርተዋል፡፡

ጄኤች ሲሜክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የማይሠራውንና በተግባር ላይ የማያውለውን ሥራ አስቀድሞ ከመናገር
በመቆጠብ፣ በተግባር ላይ አውሎ ማሳየት ተቀዳሚ ተግባሩ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ አዲስ የሚሰየመውን
ዓለም አቀፍ ብራንድ የሆነውን ስያሜ በወቅቱ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡

ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል ስያሜን የሚቀይሩት በፍርድ ቤት ውሳኔ ስላረፈበትና ተገደው ስለመሆኑ ለቀረበላቸው
ጥያቄ፣ ምንም እንኳን ማኅበሩ የሆቴሉን ስያሜ ያገኘው

የአገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መንገድ ተጉዞ በሕጋዊ መንገድ ቢሆንም፣ ‹‹ወኪል ነኝ›› የሚል ግለሰብ ክስ መመሥረቱንና
ክርክሩ በሒደት ላይ በመሆኑ፣ ከውሳኔ በፊት የሚሉት ነገር እንደሌለ በመግለጽ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ጂኤች ሲሜክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከሆቴልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት በተጨማሪ፣ በሪል እስቴት ዘርፍ
ተሰማርቶ እየሠራ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ለማሳያ ያህልም ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ
ያስገነባቸውን አፓርትመንቶችና ቪላዎች በማስተዋወቅና በመሸጥ ላይ እንደሆነ ጠቁመው፣ በቅርቡ እንደሚያስመርቅም
አሳውቀዋል፡፡
admin@hebrezema.info