1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነቡ ከሚገኙ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ከ52 ሺህ በላይ
ቤቶች በተያዘው ዓመት ሰኔ ወር ግንባታቸውንእንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

የመዲናዋ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ የቤቶቹ ግንባታ በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቅ በከተማው
አስተዳደር ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ ከተደረጉት የጋራ መኖሪያ ቤት መርሃ ግብሮች መካከል ከ50 በመቶ በላይ ተመዝጋቢዎች የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት
ፈላጊዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት፥ የመዲናዋ ነዋሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት የተጀመሩ 94 ሺህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ
ቤቶች ግንባታዎችን በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

የጽህፈት ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃረጎት ዓለሙ እንደተናገሩት፥ በግንባታ ላይ ከሚገኙ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በዘንድሮ ዓመት
ተጠናቀው ለተጠቃሚ ይተላለፋሉ ተብለው የሚጠበቁት 52 ሺህ 650 ቤቶች ናቸው።

እነዚህ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በተቀመጠላቸው ዕቅድ መሰረት የከተማ አሰተዳደሩ ግንባታቸው በቅርብ እየተከታተለ ይገኛልም ብለዋል።

ለጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ የሚፈለገው በጀትም በአጭር ጊዜ የተገኘ መሆኑ ግንባታቸውን ለማፋጠን እገዛ ማድረጉንም ተጠቁሟል።

ከ50 ሺህ በላይ ቤቶች በኮዬ ፌጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይት ነው ግንባታቸው በመፋጠን ላይ የሚገኘው።

በሌሎች የግንባታ ሳይቶች እየተገነቡ የሚገኙ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታቸው እንዲሁም እየተፋጠነ ነው።

ቤቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ሃላፊው፥ በአሁን ወቅት ግንባታቸው ከ77 በመቶ በላይ መድረሳቸውን
ተናግረዋል።

በተያዘው ዓመት መጨረሻ ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፉ ከሚጠበቁት ቤቶች በተጨማሪ በቦሌ አራብሳ፣ በጉለሌ፣ ኮልፌ እና በንፋስ ስልክ የግንባታ ሳይቶች
ላይ የሚገኙ 41 ሺህ ቤቶችም በአሁን ወቅት ግንባታቸው 41 በመቶ በላይ ደርሷል።

ለዚህም የተጀመሩ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የግብዓት እና የፋይናንስ አቅርቦቱ የተሳለጠ በመሆኑ ባለፈው ዓመት በአቅርቦት እጥረት በኩል
ተፈጥሮ የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ መቀረፉን ነው ያስታውሱት።

የግብአት እና የፋይናንስ ችግር መቀረፉ ደግሞ ቤቶቹን በማፋጠን ሂደት ያለው አስተዋጾ ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

በ20/80 መርሃ ግብር ግንባታቸው የተጀመሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማጠናቀቅ ብቻ 10 ቢሊየን ብር መመደቡን ተገልጿል።
admin@hebrezema.info
1