1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
መልካ አቴቴ የኢሬቻ በዓል ተከበረ
October 9, 2017
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ
አቅራቢያ በሚገኘው መልካ አቴቴ ዛሬ ተከብሯል።

አባ ገዳዎችና ፎሌዎች በዓሉ በሠላማዊ መንገድ እንዲከበር ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ስፍራው የመጡ አባ ገዳዎች፣ ፎሌዎች፣ ደበሌዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና የተለያዩ
የህብረተሰብ ክፍሎች ከማለዳው 12 ሰዓት ቀደም ብለው ነው በዓሉን ለመታደም በስፍራው የተገኙት።

አባ ገዳዎችም ምስጋና፣ ምርቃትና የኢሬፈና ስርዓት አከናውነው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

ከቡራዩ ለኩ ከታ በዓሉን ለመታደም የተገኙት አባ ገዳ ታከለ መለሰ ለበዓሉ አከባበር አባ ገዳዎችና ፎሌዎች ከሶስት ወራት
በላይ ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በዓሉ በመልካ አቴቴ ሳይከበር ከ29 ዓመታት በላይ ተቋርጦ መቆየቱን አስታውሰው፥ እሴቱን ጠብቆ ለትውልድ
እንዲተላለፍ አባ ገዳዎች፣ ፎሌዎችና ወጣቶች የበኩላቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመልካ አቴቴ በተከበረው ኢሬቻ የተገኙ የበዓሉ ታዳሚዎች፥ በዓሉ ሳቢና ሠላማዊ እንደነበር ገልጸዋል::

በዓሉ እሴቱን እንደጠበቀ ለትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው ጥረትም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው
የገለጹት።
admin@hebrezema.info
1