1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራደሪያ አጀንዳቸውን
ታዛቢዎች በተገኙበት ለማፅደቅ ተስማሙ።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ ያጸደቁት የታዛቢዎች የስነ ምግባር ደንብ ዘጠኝ አንቀፆችን የያዘ ነው።

ይህም የታዛቢዎችን ተግባር የሚወስንና ድርድሩን ሰለሚታዘቡበት መንገድና ታዛቢዎች ከሚዲያ ጋር የሚኖራቸውን
መስተጋብር ያቀፈ ነው።

በዚህም ታዛቢዎች አንድ የድርድር አጀንዳ ከተጠናቀቀ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ መስጠት እንደሚችሉ እና
ባላለቀ አጀንዳ መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ በደንቡ ላይ ተደንግጓል።

እንዲሁም ታዛቢዎች ከመታዘብ ውጭ አስተያየትና ሐሳብ ማቅረብ እንደማይችሉ በደንቡ ላይ ተዘርዝሯል።

በመጀመሪያ ድርድር ላይ የተሳተፈ ታዛቢም በቀጣይ በሚደረገው ድርድር ላይ ራሱ መገኘት እንዳለበትም በፀደቀው
ደንብ ላይ ተደንግጓል።

ፓርቲዎቹ በታዛቢነት በመረጧቸው 12 ዓለም አቀፍና ሃገር በቀል ተቋማትና ዲፕሎማቶች በሚገኙበት በአጀንዳ አደራጅ
ኮሚቴ ለድርደር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ለማፅደቅም ስራ ተጠናቋል ነው ያሉት።

የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያፀደቁት የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር አሰራር ደንብ ህትመት
ፓርቲዎቹ በተስማሙበት መልኩ ታትሞ የቀረበ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፥ ድንቡን በፊርማቸው አፅድቀዋል።

17ቱ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ በሚያካሄዱት ስብሰባ ታዛቢዎች በተገኙነት አጀንዳዎችን ለማፅደቅ እና
ድርድሩን በይፋ ለመጀመር ቀጠሮ ይዘው ነው የተለያዩት።
admin@hebrezema.info
1