1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
በስቶክሆልም የህዳሴው ምክር ቤትና የትግራይ ኮሚኒቲ ከስዊድን የኢፌዲሪ ኤምባሲ
ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢትዮጲያ አዲስ አመት አቀባበል ዝግጅት በደማቅ  
September 6, 2017 ተከበረ

በስቶክሆልም የህዳሴው ምክር ቤትና የትግራይ ኮሚኒቲ ከስዊድን የኢፌዲሪ ኤምባሲ
ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢትዮጲያ አዲስ አመት አቀባበል ዝግጅት ቁጥራቸው
ከ200 በላይ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ
መከበሩን በአሉ ላይ የተገኙት በኖርዲክ አገራት የኦሮሞ ልማት ማህበር ሊቀመንበር አቶ
ድሬ ሜሻል ለህብረዘማ ገልጸዋል

የኤምባሲው ተጠባባቂ ጉዳይ ፈፃሚ አቶ ለዓለም ጥላሁን በአሉን አስመልክቶ ንግግር
ያደርጉ ሲሆን አዲሱ ና መጪው አመት የሰላም የፍቅር የእድገትና የብልጽግልና
ይሆንልን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጽው ኢትዮጲያ ጥንታዊና ታሪካዊ አገር
ከመሆንዋ አንጻር የጥቁር ህዝቦች ኩራትና ተምሳሌትም ናት በለዋል
ኢትዮጲያ ላለፉት 15 አመት ወዲህ በኢኮኖሚ ከፈተኛ እድገት ያስመዘገብች ሲሆን
የአገራችን የዲሞክራሲ ግንባታም ከፍተኛ ውጠቶችን እያስመዘገበች ነው ብለዋል

በአሉ ላይ  በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የፖለቲካ
ጉዳዮች አማካሪ እና የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ክቡር አቶ ዓለም
ገብረዋህድ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለኢትዮጲያዊያኑና ትውልደ ኢትዮጲያኑ
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በበአሉ ላይ አንጋፋና በትግሉ ወቅት ከፍተኛ አውስተዋጾ የነበራቸው ታዋቂ የትግራይ
አርቲስቶች እንደነ አበበ አርዓያና በኢትዮጲያ ሶማሊ አርቲስት አሊ ባሺር ተገኝተው
ለበዓሉ ልዩ ድምቀት ሰጥተዋል
በበዓሉ ላይ ጀግና ሲናገር በሚል ርዕስ የጨረታ ስነስርዓት ተከፍቶ ለአርቲስቶቹ
ማበረታቻ አምስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ
35,220 SKK የሲዊዲሽ ኮርረነር
በላይ የተሰበሰበ መሆኑን መድረኩን ይመሩ የነበሩት የሰላም አበሻ ራዲዮና ቲቭ ደጀን
ሲውዲን አቅራቢ አቶ ፍስሃ በላይ ገልጸዋል

በተመሳሳይ ሁኔታ በተካሄደው ጫረታ በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ  ዘውትር የምትነሳው
ማህቡባ ቢሊሌ ስእል ለጨረታ ቀርቦ
6,000 ከስድስት ሺ የሲዊዲን ኮረነር በላይ ያውጣ ሲሆን በአሸናፊነት አቶ ኢብሳ
ጨፌ ተርክበዋል
በተጨማሪም በእለቱ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ
ፕሮግራምም ተካሂዷል፡፡

አቶ ኢብሳ ጨፌ በጨረታ ያሸነፉትን በኖርዲክ አገራት ለኦሮሚያ ልማት ማህበር
አበርክተዋል
admin@hebrezema.info
1