1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
የተከበሩ አባ ዱላ ገመዳ የፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

የተከበራችሁ የየገዳ አባቶች የሃይምኖት አባቶች አዛውንቶች ወጣቶች ከሁሉ በላይ በቀጥታ እየተከታተልችሁን ያላችሁ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ከሁሉ
አስቀድሜ እንኳን ለዲሱ አመት ለሽግግር የድልአመት ዋዜማ አደረሳችሁ እላለሁ

ተውዳጁና የኦሮሞው ጀግና ፕሬዝዳንታችን አቶ ለማ መገርሳ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተለያዩ ችግሮች ስላሉና በሃሊፈንት አመራር እየስጡ
ስላሉ መልዕክታቸውን እዳስተላልፍ ስለላኩኝ ከዚህ በታች የምናገረው የሳቸው መልዕክት እንደሆነ እዲታወስልኝ በመሃከላችን እዳሉ እንዲቆጠር እያልኩ
በተጨማሪም ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኤኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር ኦቦ ኡመር የኦሮሚያ ክልላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ለስፊው የኦሮሞ ህዝብ የእንኳን
አደረሳች ማልዕክታቸውን ያስተላለፉ አስቀድሜ መግለጽ እወዳለሁ።

2009 የችግር ዘመን የተገመገምንበት ዘመን እየሞትን ቀብር የጀመርንበት ዘመን ዛሬም እየሞትን ያለንበት ዘመን በተለያዩ ግምገማዎች ውስጥ አልፈን
ተገምግመን በስለን አንድነታችንን ገንብተን የምንሸጋገርበት ዘመን በርካታ ችግሮችን ያሳለፍንበት ዘመን መሆኑ ይታውቃል።

ይሁን እንጂ ይህ የጭለማ ዘመን ሊነጋ ነው የሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ድል ቅረብ ነው።

የኦሮሞ ወጣቶች ሞት የኦሮሞ አርሶ አደር ችግር በተለያዩ ከተማና ገጠር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ነዋሪዎች በተለያየ የከፋ ችግር እያለፈ ያለው
በሚመጣው አመት አንድነታችንን አጠናክረን መሰረት ባለው ትግል መሰረት ባለው ሃሳብ ልናወራ ሳይሆን ልናሸንፍ ለመዋጋት ሳይሆን ልናሽንፍ እንደ ኦሮሞ
ባህል የታውቁ ስልቶችን ከአንድ አመራር በማመንጨት ህዛብችንን ለማሸጋገር እውንውታዊ ዲሞክራሲን እውንውታዊ ሰላምን እውነታዊ አንድነትን በዚህ
አገር ውስጥ ለማምጣት የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እያደረገ ያለውን ትግል ከምን ግዜውም የበለጠ ጠንክሮ የሚቀጥል መሆኑን
ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።

ኦሮሞ ማቅፍን ያውቃል፣ ማኖርን ያውቃል፣ ኦሮሞ ግለኝነት የለውም ….ማጭድ ጤፍ ስታጭድ ሁሉን ለኔ ትላለች ያንን ያጨደችውን መቼም
አትጠቀምበትም  የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ታጋዮች ከግለኝነት ውስጥ ወጥተን  ትግላችን በአንድነት ለህዝባች እንዲሆን አዲስ ቃል
ኪዳን ለህዝባችን እንደምንገባ ለህዝባችን መግለጽ እወዳለሁ

መቸገር ለኦሮሞ አዲስ አይደለም መሞት ለኦሮሞ አዲስ አይደለም ታሪክ መስራት ለኦሮሞ አዲስ አይደለም የተለያዩ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ መታሰር ሊኖር
ይችላል የተለያየ ሞት ሊኖር ይችላል ለህዝባችን እስከጠቀመ ድረስ ግንባራችንን ሰጥተን አንድ ግዜ ሳይሆን አስር ግዜ በመሞት የኦሮምን ህዝብ ድል ከግቡ
ለማድረስ ከሁሉ በላይ አንድነታችን ወሳኝ ነው ሰው እንፈራለን ሰው ስለሆን እንጠራጠራለን ስጋን ስለለበስን እንሰጋለን ለማንም ግን ሞት አይቀርም

ኦሮሞ በታሪኩ ውስጥ የጀመረውን ይጨርሳል አዲስ  የተሸነፈ ታሪክ ሰንካላ ታሪክ የኦሮሞው ወጣት ከውስጡ በማውጣት የድል አመለካከት….. ሊሸጋገር
የሚችል አመለካከት በአንድነት ላይ የተመሰረተ አመለካከት እንደ ኦሮሞ…… እንደ ኦሮሞ ታሪክና ባህል እውን ማድረግ ከሁላችን የሚጠበቅ ይሆናል።

ኦሮሞ ከብቶች ያግዳል አገራችን አንድ የምትታለብ ላም ጥጃዋ (ልጇ) ከሞተ እንድትታለብ ብላችሁ የሌላ ላም ልጅ አምጥታችሁ ብታስጠጉት ረግጣ
ታባርረዋለች ታድያ አባቶቻችን ምን ያደርጋሉ ከሞተው ልጇ ቆዳውን ገፈው እንዳይደርቅ አድርገው አዲሱን ጥጃ አልብሰው ላሟ ስታሸተው የልጇ መስሏት
እንድታጠባው ያደርጋሉ
ኦሮሞ የሚጠቅመውን የሚበጀውን የራሱ የሆነን ስለሚያውቅ ዳራው ወይም መስረቱ አካሄዱና መስመሩ ለህዝባችን በማይጠቅም ጉዳይ ላይ ጊዜችንን
ማጥፋት አያስፈልግም በዚህ አመት የኦሮሞ ህዝብ አንድነት የኢትዮጲያ አንድነት የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን (ኦህዴድ) አንድነት ለመናድ
ምንጫቸው የማይታወቅ የተለያዩ ማህበርሰብ ሚዲያዎች (መገናኛ ብዙሃን) ባለቤታቸው የማይታወቅ በስማችን በቋንቋችን እኛን ሊከፋፍል የሚችል ብዙ
መልዕክት ያሰትላልፋሉ።

አንተ ኦሮሞ ንቃ ከአንድነት ውጪ ድል የሚባል የለም መልእክቱ ከየትም ሊመጣ ይችላል ያ ሚመጣው መልእክት ለአንድነታችን እንቅፋት ከመሆን ውጪ
ከማይታወቅ ምንጭ ወሬ በመውሰድ ድ
ችንን ወደዚያ ለማራቅ በሚደረግ እንቅስቃሴ እኛ የምናደርገው ተሳትፎ  ከፍተኛ ጥንቃቄ መሆን አለበት።

በዚህ አመት ለሚዲያ የተለየ ትኩረት  የሰጠነው ሚዲያ ማንነትትን ለማስተዋወቅ የራስን ባህልና ታሪክን ለማሳየት የተጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ ትልቅ
ሚና ሊጫወት ይችላል በአለም ታርክ ውስጥ እንደሚዲያ በፍጥነት ያደገ የለም የእልምናና የክርስትያን እምነት ከ አንድ ሺ አመት በላይ ትልቅ ገንዘብና
መዋቅር በአልም ደረጃ ቢሰራም እንኳን እስከ አሁን ከ ሁለት ቢሊዮን የበለጠ ሰው የላቸውም።

ካንሰር (ነቀርሳ) ኤች አይ ቢ (HIV)የተለያዩ በሽታዎች የተለያየ ቴክኖሎጂ በመቶ አመት ውስጥ ምን ያህል በፍጥነት ማደግ ቢችል
አንድ ቢልዮን
ልደርስ አልቻለም ሶሻል ሚዲያ በስምንት አመት ውስጥ በአለም ደረጃ በአዲስ መልኩ ሁለት ቢሊዮን ከግማሽ ሊዳረስ ችሏል ይህ አዲስ ታሪክ ነው በዚህ
ታርክ ውስ
በመጠቀም ህዝብችንን ማንቃት አንድነታችንን ማጠናከር ለመተራረም ለመማማር ለመሻገርና ለማሻገር እንድንጠቀምበት የኦሮሚያ ክልላዊ
መንግስት የተለየ ትኩረት በመስጠት ይህን ሚዲያ ለማሳደግ ለማጠናከር ወስኗል ::

ምክንያቱም የተለያዩ ሰዎች ምንጩ ባልታወቀ ወሬ አንድነታችንን ብቻ ሳይሆን ሰላምችንን ለማደፍረስ ልማታችንን ለማቆም እየተጠቅሙበት ስለሆነ
.....ይህ ሚዲያ የኦሮሞ ህዝብ ሚዲያ ነው ይህ ሚዲያ የኦሮሞ ወጣቶች ሚዲያ ነው ተጠቀሙበት ምሩት ምከሩት መስመር አሳዩት ካጠገቡ አትሂዱ
በናንተው ገነዘብ ከሁሉ አርሶ አደር ሰብስበን እየገነባነው ነው ገንዘባችሁ ብቻ ሳይሆን ሃሳባችሁም እዛው ውስጥ ስለሚንጸባረቅ በዚህ ሚዲያ በመጠቀም
የኦሮሞን ፍላጎትና ጥቅምን ከግብ ለማድረስ ከምንግዜውም በበለጠ በአንድነት እንድንሰራ መልዕክቴን ማስተላለፍ እወዳለሁ።

2010 አመተ ምህረት አንድነት የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን (ኦህዴድ)ከላይ እስከታች መዋቅሩን በማጠናከር የኦሮሞን አዋቂዎች ምክር
በመውሰድ ከገዳ አባቶች ተቀራርቦ የኦሮሞን ታሪካ ባህልን በመማር ህዝባዊ ድርጅት መሆኑ ለህዝባዊ ድል እንደሚታገል እውን ያደርጋል ይህን ድርጅታችን
ቃል ይገባላችኋል።

ኦሮሞው እንደባህሉ በውስጡ ለሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦች ብቻ ሳይሆን የውጪ ሰዎች ክልችን መጥተው ከኛ ጋር ለመኖር የፍለጉ ሁሉ እንደ ገዳ ስርዓት አቅፎ
አብሮ ለመኖር ዝግጁ ነው በዚህ አመት እየታየ ያለው የኦሮሞ ጠላት በኦሮሞና በኦሮሚያ ላይ ያለው ጥርጣረ እየሰፋ ነው ትንሹም ትልቁም ኦሮሞንና
ኦሮሚያን ይጠራጠራል ኦሮሞና
ኦሮሚያ የኢትዮጲያ ዋልታ ምሰሶ ነው ኢትዮጲያን እናጠናክራልን እናሳድጋለን በደስታም እንኖራለን ከኢትዮጲያ ግራና ቀኝ
መሄድን አናስብም ኢትዮጲያ ውስጥ እኩሉነት ዲሞክራሲያዊነት ሰላምና ልማት ተስተካክሎ እንዲኖር ደግሞ ትግላችንን እንቀጥላለን።

እናንተ ይህን ክልልና ሕዝብ አለቅጥ ለምትጠራጠሩ ሰዎች ኦሮሞ ማቀፍን ያውቃል ማኖርን ያውቃል ማጉረስን ያውቃል ማብላትን ያውቃል አታስቡ በሰላም
ከኛ ጋር መኖር ትችላላችሁ  ህዝባችንን ለመከፋፈል ድርጅታችንን ለመከፋፈል ከብሄር ብሄረሰቦች ጋር ልትነጣጥሉን የተለያየ ሙከራ የምታደርጉ ጠላቶቻችን
ኦሮሞ አዋቂ ነው ሽማግሌዎችን ይሰማል ምክር ይሰማል ኦሮሞ ለወሬ ብቻ ሳይሆን ለድርጊት ይታገላል  አንፈርስም አንበታተንም ወደ ኋላ አንመለስም
እንጠነክራለን እንታገላለን ድል ቅርባችን ነች የትኛውም ጠላት ሊያቆምን አይችልም።

የኦሮሞ ወጣት በመጪው አመት አላስፈላጊ የሆነ ሞት አልባሌ መስዋዕትነት መክፈል አይገባችሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማስተዋል መደማመጥ እንደ ኦሮሞ
ታሪክና ባህል በ አድምጠኝ ላድምጥህ በመነጋገር መጭውን ዘመን ብሩህ ዘመን የድል ዘመን የምንሻገርበት ዘምን እንጂ የምናዝንበት እንዳይሆን የኦሮሞ
ውጣቶች ከሁሉ በላይ የሚጠበቅባችሁ ስራ እንድትሰሩ መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።

በመጨረሻም አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳት አሁን እየሰሩ ያሉትን ስራ በድል አጠናቀው በጥቂት ቅናት ውስጥ ለሰፊው የኦሮሞ
ህዝብ መልእክታቸውን ስለሚያስተላልፉ እኔ አሁን ያስተላለፍኩት መልእክት
የኦሮሚያ ክላልላዊ መንግስት መልእክት መሆኑና የተወዳጁ ፐሬስዳንት አቶ ለማ
መገርሳ መሆኑን ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እንዲያውቀው እፈልጋለሁ

ድል የኦሮሞ ትሆናለች
www.heberezema.info
admin@hebrezema.info
1