1
States
Investment
Tourism
Sport
Entertainm.
Radio & Tv  
About us
Contact  
Links
admin@hebrezema.info
Archives  
የኦሮሚያ ክልል ጥሪት ያፈሩ አርሶና አርብቶ አደሮችን ወደ
ኢንቨስተርነት የማሳደግ አሰራር መተግበር ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2012 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል በተለያየ መልኩ ጥሪት ያፈሩና አቅም የፈጠሩ አርሶና አርብቶ
አደሮችን ወደ ኢንቨስተርነት ማሳደግ የሚያስችለውን መመሪያ አዘጋጅቶ መተግበር መጀመሩን አስታወቀ።

ክልሉ አጠቃላይ ወቅታዊ የኢንቨስትመንት አሰራሮች መሻሻል ን አስመልከቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊና የክልሉ ኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዳባ ደበሌ ባለፉት ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ኢኮኖሚ
ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

“በዋናነት የኢንቨስትመንት ሴክተሩን ማጠናከር ቀዳሚ መሆኑ ታውቆ ዘርፉን የማሻሻል ሥራ ተከናውኗል” ብለዋል።

እንደ አቶ ዳባ ገለጻ በክልሉ ከ11 ሺህ በላይ ኢንቨስትመንቶች ያሉ ሲሆን 51 በመቶ የሚሆኑት በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ
ናቸው።

በተጨማሪም 12 በመቶ በግብርና ዘርፍ፣ 18 በመቶ የግብርና ምርት በማቀነባበር እንዲሁም 17 በመቶ የሚሆኑት
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የባለሃብቶች አጠቃላይ ሁኔታን ሲያብራሩም “92 በመቶ የአገር ውስጥ በለሃብቶች፣ 3 ነጥብ 2 በመቶ ዲያስፖራ እና አራት
በመቶ የውጪ አገር ዜጎች ናቸው” ብለዋል።

ይሁን እንጂ በተለያየ መንገድ ጥሪት ያፈሩ አርሶና አርብቶ አደሮች እስካሁን በኢንቨስትመንት ዘርፉ በስፋት
እንዳልተሰማሩም ነው አቶ ዳባ የገለጹት።

“የክልሉ መንግስት ይህን ለማስተካከልና ሌሎች የኢንቨስትመንት ማነቆዎችን ለመፍታት የሕግ ማሻሻያዎችን አድርጓል” ሲሉም
ተናግሯል።

ከነዚህ ውስጥ አርሶና አርብቶ አደሩ ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገባ የሊዝና የመሬት ኪራይ ክፍያ ነጻ የሚያደርግለት መመሪያ
መውጣቱን ነው በማሳያነት የጠቀሱት።

ከዚህ ባለፈ በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው በተለያየ ዘርፍ ወደምርት ሥራ የገቡ የክልሉ ወጣቶችም የሚበረታቱበት መመሪያ
መተግበር መጀመሩን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ዳባ ገለጻ የሕጉ መሻሻል ትክክለኛ አልሚ ባለሃብቶች ያለምንም እንግልት ወደሥራ እንዲገቡ ያደርጋል።

በክልሉ ከዚህ በፊት እንደ ችግር ይነሳ የነበረው የካሳ አከፋፈል ስርዓትና መጠንም መስተካከሉን ገልጸው የኢንቨስትመንት
ስርጭትም ከመሀል አገር ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰፋበት ሁኔታ መመቻቸቱን ጠቁመዋል።

”ዘርፉ ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር አስችሏል” ያሉት ደግሞ የክልሎ
ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ ጃልዴ ናቸው።

“ኢንቨስትመንት የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ የውጪ ምንዛሬ የሚያመጣና ለቴክኖሎጂ ሽግግር በር የሚከፍት በመሆኑ ልዩ ትኩረት
ተሰጥቷል” ይላሉ።

አቶ ኃይሉ እንዳሉት የዘርፉ ማነቆ ሆነው የቆዩ የአሰራር ችግሮችን በመሰረታዊነት የመፍታት ሥራ ለመስራት የኢንቨስትመንት
አስተዳደር ደንቡም እንዲሻሻል ተደርጓል።
ይህም ባለሃብቶች ብዙ ሳይንገላቱ አስፈላጊውን
አገልግሎት እንዲያገኙ የአንድ መስኮት አገልግሎት
እንዲጀመር ማድረጉን ነው ያስረዱት።

“የአንድ መስኮት አገልግሎት ደግሞ 12 ሴክተር
መስሪያቤቶች በአንድ ማዕከል ላይ እንዲገኙ
አስችሏልም” ብለዋል ኃላፊው።

በክልሉ ከ3 ነጥብ 10 ቢሊዮን ብር የሚገመት
የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በመከናወን ላይ
መሆናቸው ተመልክቷል።

ከዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ወደ ምርት የገቡ
ኢንቨስትመንቶች ሲሆኑ የተቀሩት በሂደት ላይ
መሆናቸው ተገልጿል።
    Home             News          States         Investment   Tourism         Sport          Entertainm.      Radio & Tv     About us        Contact      Links                  Archives
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
1