ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ የአምቦ-ጉደር እና ሸነን-ሰዮ የአስፋልት መንገድ ኘሮጀክት ግንባታን አስጀመሩ
15 February 2021
|
Home News States Investment Tourism Sport Entertainm. Radio & Tv About us Contact Links Archives
|
HEBREZEMA.INFO INDEPENDENT NEWS & MEDIA DESIGNED BY ZEWDU TEKLU © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
|
ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ 110 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን የአምቦ-ጉደር እና ሸነን-ሰዮ የአስፋልት መንገድ ኘሮጀክት
ግንባታ በዛሬው እለት አስጀምረዋል።
ለመንገዶቹ ግንባታ በአጠቃላይ 4.6 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን የግንባታው ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት በጀት
የሚሸፈ ነው።
መንገዶቹ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እና በኦሮሚያ ኮንስትራክሽ ኮርፖሬሽን ተቋራጮች ይገነባሉ።
ሁለቱም መንገዶች በ5 ዓመት ውስጥ ተገንብትው ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የነጻነት ተምሳሌት በሆነችው የአምቦ ከተማ የአምቦ-ጉደር እና የጉደር-ሰዮ-ሸነን የመንገድ ግንባታን
አስጀምረናል፤ የአምቦ ሕዝብ፣ በተለይም ደግሞ ወጣቱ፣ እነዚህን እመርታዎች እንደሚጠቀምባቸው እና ለዘላቂና
ጠቃሚ ልማት መነሻ እንደሚያደርጋቸው እምነቴ ነው" ብለዋል።
"የአምቦ-ጉደር 18.5 ኪ.ሜ. መንገድ እና የጉደር-ሰዮ-ሸነን 91.8 ኪ.ሜ. የመንገድ ፕሮጀክቶች ዛሬ በአምቦ ከተማ
ከተጀመሩት መንገዶች መካከል ሦስተኛ ናቸው" ያሉት ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ "በአጠቃላይ በ4.6 ቢሊየን
ብር የሚገነቡት እነዚህ መንገዶች የአካባቢውን ነዋሪዎች ጥያቄ የሚመልሱ ናቸው" ብለዋል።
በተስፋዬ ለሜሳ