1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
አዳማ ሀምሌ 9/2009 በዘጠኝ ወራት ውስጥ አዲስ አበባን የጎበኙ 650 ሺህ የውጭ አገር ቱሪስቶች በቆይታቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ ከ31
ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ገብረፃዲቅ ሃጎስ እንደገለፁት በዓመቱ 675 ሺህ የውጭ ቱሪስቶች አዲስ አበባ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ እቅድ
የተያዘ ቢሆንም እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት ድረስ በ650 ሺህ  ቱሪስቶች ጎብኝተዋል፡፡

ቱሪስቶቹ ከጎበኙዋቸው የመስህብ ስፍራዎች መካከል ብሄራዊ ሙዚየምና እንጦጦን ጨምሮ 13 የአዲስ አበባ ባህላዊና ታሪካዊ ስፍራዎችና መዳረሻዎች
ይገኙበታል ።

የቱሪስቶቹ ቆይታ በአማካኝ  12 ቀናት መድረሱንና ለአልጋ ፣ ለሆቴል መስተንግዶ ፣ ለአስጎብኚዎች ክፍያ ፣ ለባህላዊ ቁሳቁሶች ግዥና ለሌሎች አገልግሎቶች
ከ31 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርገዋል ።

የቱሪዝም ፍሰቱን ለማሳለጥ ቢሮው  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 720 ጎብኚዎች የሚመሩበት መፅሃፍና ካርታ  አዘጋጅቶ አሰራጭቷል ።

ወደ ከተማዋ የሚገባ ቱሪስት ያለማንም አስጎብኚ ጭምር ከተማዋን መጎብኘት እንዲችል የአዲስ አበባን የተለያዩ ቦታዎች የሚያሳይ የቱሪስት ካርታ
በተመረጡ 17 ቦታዎች ላይ ተተክሎ ስራ ላይ መዋሉን ጠቁመዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ ቢሮው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የከተማዋን ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን ለማበልጸግ ጥረት አድርጓል።

በተለይ ባህልና ኪነ-ጥበብን ዋንኛ የልማት ኃይል በማድረግ የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን
ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

በቱሪዝም ዘርፍ ነባር ቅርሶችን የመጠገንና አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት  አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ገብረፃዲቅ አስረድተዋል።

በዚህ ረገድ በዚህ ዓመት ሙሉ በሙሉ እድሳት ተደርጎላቸው ስራ ከጀመሩት ነባር ቅርሶች መካከል የአዲስ አበባ ሙዚየም፣ የድልና የሰማእታት  ሐውልቶች
ይጠቀሳሉ።

የራስ ቴያትር ቤትን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአዲስ መልክ ለመገንባት ቢታቀድም በወሰን ማስከበርና በተለያየ ምክንያት አለመጀመሩ በበጀት ዓመቱ
ካጋጠሙ እጥረቶች መካከል ተጠቃሽ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል ።

በቢሾፍቱ ከተማ ትናንት በተጀመረውና ለአራት ቀናት በሚካሄደው መድረክ ላይ ከወረዳ እስከ ማዕከል የሚገኙ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ አመራሮችና ባለድርሻ
አካላት ተሳትፈዋል፡፡
admin@hebrezema.info
1