1
States
Investment
Tourism
Sport
Entertainm.
Radio & Tv  
About us
Contact  
Links
admin@hebrezema.info
Archives  
የተለያዩ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ድጋፋቸውን አጠናክረው
ቀጥለዋል
አዲስ አበባ ሚያዝያ 15/2012 (ኢዜአ) የተለያዩ ድርጅቶችና ባለሀብቶች በአዲስ አበባ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት
የሚያግዝ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ለከተማ አስተዳደሩ አስረከቡ።
ከተማ አስተዳደሩ ድጋፉን ዛሬ ሲረከብ እንደተገለጸው የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ያደረጉት 49 የተለያዩ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ናችው።

ከእነዚህ መካከል የተለያዩ ማህበራት፣ የገበያ ማዕከላት፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ሞሎች እና ግለሰቦች ይገኙበታል።
ድጋፉ በገንዘብ፣ በዓይነትና በአገልግሎት የሚለካ ሲሆን ገንዘቡ ከ2 ነጥብ 36 ሚሊዮን በላይ ብር ነው።

ከእዚህ በተጨማሪ ግምቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ምግብና ቁሳቁስ እንዲሁም የተለያዩ ነጻ አገልግሎቶችና ለኳራንታይን የሚያገለግሉ ሕንጻዎችም
በድጋፉ ተካተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት የቤት ኪራይ ቅናሽ ያደረጉ ድርጅቶችም በድጋፉ ይገኙበታል።

ድጋፉን የተረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ስጦታውን ላቀረቡት ባለሃብቶችና የድርጅት ተወካዮች ምስጋና  
አቅርበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍና ግንዛቤ በመፍጠር የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የጀመረው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል።

በቀጣይም “የኮሮናቫይረስ በአገራችን ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመመከት ትብብራችን መቀጠል አለበት” ሲሉ ከንቲባው መልዕክት አስተላልፈዋል።
    Home             News          States         Investment   Tourism         Sport          Entertainm.      Radio & Tv     About us        Contact      Links                  Archives
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
1