ትዊተርን ለፐብሊክ ዲፕሎማሲ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተዘጋጀ ፕሮፖዛል ትውውቅ ተደረገ

July 29,2021

በኖርዲክ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ትዊተርን ለፐብሊክ ዲፕሎማሲ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያዘጋጁትን ፕሮፖዛል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ሃላፊዎች በተገኙበት በበይነ መረብ አስተዋወቁ።


ነዋሪነታቸውን በኖርዌይና ስዊድን ያደረጉትና በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ እንዲሁም ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ከፍተኛ ባለሙያዎች የሆኑት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ሀገራቸውን ለማገልገል ልዩ ልዩ የድጋፍ ተግባራት ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን አንስተው፣ በተለይም የህግ ማስከበር ስራ ከተጀመረ ወዲህ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት በዲጂታል ሚዲያ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትና የፈጠሩት ተጽእኖ ይህን ፕሮፖዛል እንዲያዘጋጁ እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል።


ትዊተርን ለፐብሊክ ዲፕሎማሲ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተዘጋጀ ፕሮፖዛል ትውውቅ ተደረገ በኖርዲክ ሃገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ትዊተርን ለፐብሊክ ዲፕሎማሲ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያዘጋጁትን ፕሮፖዛል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ሃላፊዎች በተገኙበት በበይነ መረብ አስተዋወቁ።


ነዋሪነታቸውን በኖርዌይና ስዊድን ያደረጉትና በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ እንዲሁም ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ከፍተኛ ባለሙያዎች የሆኑት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ሃገራቸውን ለማገልገል ልዩ ልዩ የድጋፍ ተግባራት ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን አንስተው፣ በተለይም የህግ ማስከበር ስራ ከተጀመረ ወዲህ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት በዲጂታል ሚዲያ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትና የፈጠሩት ተጽእኖ ይህን ፕሮፖዛል እንዲያዘጋጁ እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል።


ባለሙያዎቹ አክለውም በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ አካላት ባልተቀናጀና በተበታተነ መልኩ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው በዲጂታሉ ዓለም ላይ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አዎንታዊ ትርክቶች ትኩረት ማግኘት እንዳልቻሉ፣ በአንጻሩ ደግሞ በተቃራኒው የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተጨበጠ ነገር ግን በተቀናጀና በተደራጀ የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም የሃገሪቱን ገጽታ በማበላሸት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል። በመሆኑም ይህን ችግር ለመፍታት መከናወን ያለባቸው ዝርዝር ተባራትን የሚያመላክተውንና በቡድኑ አባላት የተዘጋጀውን ፕሮፖዛል አቅርበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የቡድኑ አባላት ስላቀረቡት ፕሮፖዛልና ስላሳዩት ተነሳሽነት አመስግነው፣ እንደ ሃገር የገጠሙንን ፈተናዎች በመወጣት ረገድ የትዊተር ዲፕሎማሲን በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ መጠቀም አስተዋጽኦው እንደሚኖረው ገልጸዋል።


አክለውም ከጉዳዩ ወቅታዊነትና ከሚያስከኘው ጠቀሜታ አንጻር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቡድኑ አባላት ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊትም በበኩላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በራሳቸው ተነሳሽነት ጥናት አድርገውና ሰነድ አዘጋጅተው ሃገራቸውን በዕውቀትና ክህሎት ሽግግር ለማገዝ በመንቀሳቀሳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ኤጀንሲው ቡድኑ ያዘጋጀው ፕሮፖዛል በባለድርሻ አካላት እንዲታወቅ ከማድረግ በተጨማሪ ሰነዱ የስራ መሳሪያ ሆኖ የሃገራችንን የትዊተር ዲፕሎማሲ ደረጃ እንዲያሻሽል ክትትል እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።