1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
ፕሬዚዳንት አል በሽር በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
April 2, 2017
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽር በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ
ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው፥ ፕሬዚዳንቱ ከነገ በስቲያ ማክሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ።

በቆይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሏል።

መሪዎቹ በሃገራቱ የሁለትዮሽ እና የጋራ ጉዳዮች ላይ በተለይም ሁለቱ ሃገሮች በፈረሟቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ላይ
ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ሃገራቱ በተፈራረሟቸው ስምምነቶች አተገባበር ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በመምከር የመፍትሄ ሃሳቦችን
ያስቀምጣሉ ተብሎ አንደሚጠበቅም ነው መረጃው የጠቀሰው።

በውይይታቸው መጨረሻም የሃገራቱን የቆየ ወዳጅነትና ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን የሚያሳድጉ ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙም
ነው የሚጠበቀው።

ፕሬዚዳንት በሽርም በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመጎብኘት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ያጠናቅቃሉ።

ኢትዮጵያና ሱዳን በሃይል ዘርፍ፣ በፀጥታና ደህንነት እንዲሁም መሰረተ ልማትን ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች የትብብር ስምምነቶችን
ደርሰዋል።
admin@hebrezema.info
1