1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
admin@hebrezema.info
1
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርቡ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ አገራት የተሹሙ አምባሳደሮች ዛሬ በብሔራዊ
ቤተ መንግስት ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የተገኙ ሲሆን፥ ለአምባሳደሮቹ የስራ
መመሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደሮቹ በሚሄዱባቸው አገራት ሁሉ በቅንነትና በታማኝነት ኢትዮጵያን እንዲያገለግሉ ፕሬዚዳንት ሙላቱ አሳስበዋል።

በስራቸውም ስኬት እንዲገጥማቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው አምባሳደሮቹ በጠንካራ የስራ ተነሳሽነት ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ
መድረኮች ከፍ ለማድረግ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

አምባሳደሮቹም በየተመደቡባቸው አገራት የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ በተለይ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ረገድ ስኬታማ
ትግባራትን ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአምባሳደሮቹ የቃለ መሃላ መርሃ ግብር ከተካሄደና የስራ መመሪያ ከተሰጠ በኋላ መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ
ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የሾሟቸው አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራትም ዝርዝርም፦

1. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን - አሜሪካ ዋሽንግተን

2. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ - ቻይና ቤጂንግ

3. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አስቴር ማሞ - ካናዳ ኦታዋ

4. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም - ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ

5. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና - ስዊድን ስቶኮልም

6. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተበጀ በርኼ - የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ አቡ ዳቢ

7. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ - ኳታር ዶሃ

8. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ - ኢንዶኔዥያ ጃካርታ

9. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ - ሩዋንዳ ኪጋሊ

10. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዓሊ ሱሌይማን - ፈረንሳይ ፓሪስ

11. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉጌታ ዘውዴ - ሱዳን ካርቱም

12. አምባሳደር እውነቱ ብላታ - ቤልጂዬም ብራስልስ ነው።