1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
18 የዲፕሎማሲ ተቋማት ለበርካታ ዓመታት አጥረው የያዙትን መሬት እንዲያስረክቡ
ሊደረግ ነው
April 10, 2018
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 18 የዲፕሎማሲ ተቋማት ለበርካታ ዓመታት አጥረው የያዙትን
ይዞታ እንዲያስረክቡ ለማድረግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር መወያየቱን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት
ቢሮ አስታወቀ።

የዲፕሎማሲ ተቋማት ለማልማት ሲዘጋጁ ሌላ መሬት እንዲዘጋጅላቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር መወያየቱን
አስታውቋል።

ለበርካታ ዓመታት ባዶ መሬት አጥረው የያዙትን የዲፕሎማሲ ተቋማት መካከል የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ አንዱ ሲሆን፥
ለ23 ዓመታት አጥሮ የያዘው መሬት መኖሩን ቢሮው ጠቅሷል።

ቢሮ ይህን ያላው የ9 ወር አፈፃጸሙን ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ጀማል አሊ ለምክር ቤቱ ማዘጋጃ ቤታዊ ቋሚ ኮሚቴ እንደተናገሩት፥ በመዲናዋ በኤንባሲዎችና አለም
አቀፍ ተቋማት ተይዘው ለበርካታ አመታት ሳይለሙ የቆዩ 18 ይዞታዎችን እንዲያስረክቡ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር
ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡

ለልማት መሬት አጥረው ከቆዩት ኢንባሲዎቼ መካከል የህንድ ኢንባሲ ብቻ ወደ ልማት እየገባ መሆኑን ነው አቶ ጀማል
የተናገሩት።

የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው በሊዝ መሬት ከወሰዱ 7 ሺህ 259 ባለይዞታዎች
መካከል በ244 ባለይዞታዎች ላይ እርምጃና ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ተነግሯል።

እንዲሁም በውላቸው መሰረት ክፍያ ባልፈፀሙ 21 ባለይዞታዎች ላይ ክስ እንደተመሰረተባቸው ተገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ልማት ሳይገቡ ታጥረው በቆዩ 49 የመሬት ባላይዞታዎች ላይም
እርምጃ ተወስዷል ።

ሌሎች ወደ ልማት ያልገቡ 138 ይዞዎች የተለዩ ሲሆን፥ ከዚህም መካከል 16 ኤምባሲዎች፣ 2 ዓለም አቀፍ ተቋማት፣
25 የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ተቋማት እንደሚገኙበትም ተነግሯል።

በሌላ በኩል የስድስት ወር ጊዜ ተሰጥቶዋቸው ከነበሩ 120 ባለይዞታዎች መካከል በ32 ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፥
የ23 የግል ባለይዞታዎችን ውልን በማቋረጥ 17 ነጥብ 9 ሄክታር ወደ መሬት ባንክ እንደገባ ታውቋል።


በታሪክ አዱኛ
admin@hebrezema.info
1