1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የተከሰተው ግጭት የሁለቱን ክልሎች ህዝብና መንግስት አይወክልም-
የክልሎቹ ርዕሰ መስተዳድሮች
September 17, 2017
አዲስ አበባ መስከረም 7/2010 በኦሮሚያና  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት
የሁለቱን ክልሎች ህዝብና መንግስት እንደማይወክል የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች አስታወቁ።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሐመድ
ግጭቱን አስመልክቶ በአዲስ አበባ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሁለቱም ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረው ክስተት የሁለቱን
ክልል ህዝብና መንግስት የማይወክል ድርጊት ነው።

ድርጊቱን ያወገዙት ርዕሰ መስተዳድሮቹ ግጭቱን በአፋጣኝ በማስቆም ፣በግጭቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን  መልሶ ለማቋቋምና
በግጭቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትንም
ተመኝተዋል።

የዚህን ዜና ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
admin@hebrezema.info
1
https://www.facebook.com/hebre.zema/videos/1590415107645352/ https://www.facebook.com/hebre.zema/videos/1590417440978452/