1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
በአዲስ አበባ ሙስናና ብልሹ አሰራር የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታን እያጓተተ ነው- ጥናት
April 24, 2018
አዲስ አበባ ሚያዚያ 16 2010 (ኤፍ ቢሲ) በመዲናዋ እየተካሄደ ያለውን የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሙስና እና
ብልሹ አሰራር እያጓተተው እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከ።

የፌደራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባዘጋጀው ውይይት ወቅት ነው ይህ የተነገረው።

በውይይት ለቤቶቹ መዘግየት የተላለዩ ምክንያቶች የተጠቀሱ ሲሆን፥ በዋነኝነት የቤት ልማቱ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር
ተጋላጭ መሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

የቤት ልማቱ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የተጋለጠባችው መንገዶች የውይይት መድረኩ በ18 ዋና ዋና ነጥቦች
አስቀምጧቸዋል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከዚህ በፊት በተደረጉ ጥናቶች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታን እያጓተተ መሆኑ ቢገለፅም
ችግሮቹን ለመቅረፍ የተሰራው ስራ በጣም ዝቅተኛ እንድሆነ በውይይቱ ተነስቷል።

በዚህም የተመዝጋቢዎች መረጃ አያያዝ እና አሰራር ላይ የሚታየው ክፍተት ተነስቷል፤ እንደ ጥናቱ ከዚህ በፊት
ተመዝጋቢዎች ስለምዝገባው ሂደት እንዲያቁ የሚያደርግ ስርዓት ያልተዘረጋ እና በመረጃ ቋት ያልተደገፈ መሆኑ
ተነስቷል።

ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት በ2005 ዳግም ምዝገባ ቢካሄድም በ1997 ተመዝግበው የነበሩት በዳግም ምዝገባ ወቅት
ስም ዝርዝራቸው ባለመገኘቱ   ቅሬታ እንዳቀረቡ በውይይቱ ተነስቷል።

እንዲሁም የግል መኖሪያ ቤት ያለቸውን እና የልማት ተነሽዎችን የመመዝገብ እና የማጣራቱ ስራ ላይ ያለው ክፍተት
የቤት ልማቱን ለሙስና እና ብልሹ አሰራር አጋልጧል ተብሏል።

በዚህም የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው የኮንዶምንየም ቤት የደረሳቸው በርካታ ሰዎች እንደሚገኙ ለማሳያነት ተጠቅሷል።

በሌላ በኩል የዲዛይን ክለሳ እና  ባልተጠበቀ ዲዛይን ግንባታ መፈፀም የግንባታ ጊዜ እያራዘሙና እና መንግስትን
ላልተፈለገ ወጪ እየዳረጉ እንድሆነም ተነስቷል።

የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሳይጠናቀቁ እጣ የሚወጣላቸው የቤት ባለዕድለኞች ዘንድም የሚነሳው ቅሬታ ሌላው
የሙስና እና ብልሹ አሰራር መገለጫ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ክፍተት እንዳለም ተነግራል።

እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች የቤት እድለኛ በሚሆኑበት ወቅት ክፍያ ለመፈፀም እቅም ስለሚያጡ ወደ ሌሎች
ለማስተላለፍ እንደሚገደዱ ጥናቱ አመልክቷል።

ከዚህ ባለፈ በቤት ልማቱ ያልተከፈለ እና ያልተሰበሰበ ሂሳብ እንዳለ ይነሳል።

ከከተማዋ ቤቶች ልማት አስተዳድር ቢሮ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት እና ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት በኮልፌ
ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተደረገ ኦዲት 295 ሚሊየን ብር

በላይ ተመላሽ መደረግ እያለበት እስካሁን ተመላሽ የተደረገው 189 ሚሊየን ብር ብቻ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ቅድመ ክፍያ ወስደው ጥለው ከሚጠፉ እና ከሀገር ከሚወጡት ተቋራጮች አድራሻቸውን ፈልጎ ቅድመ ክፍያውን
የማስመለሱ ስራ ክፍተት እንዳለበት ተነስቷል።

እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች መላላትም ሌላው የተነሳ ክፍተት ነው።

ከ1997 ጀምሮ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን 759 ሺህ 232 የመዲናዋ ነዋሪዎች እንድተመዘገቡ ነው
መረጃዎች የሚጠቁሙት።

በዚህም 400 ሺህ (83) በመቶዎቹ መኖሪያ ቤት ለማግኘት እየቆጠቡ የሚገኙ ሲሆን፥ 128 ሺህ ተመዝጋቢዎች
በተለያዩ ምክንያቶች ቁጠባቸውን እንዳቋረጡ ተጠቁሟል።

እስካሁን ባለው ሂዲት እስከ 177 ሺህ የመዲናዋ ነዋሪዎች በጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

ዛሬ በተካሄደው ውይይት እንደተነገረው 400 ሺህ የሚሆኑ ተመዝጋቢዎች ለ10 አመት የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ
ለመሆን እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።በፋሲካው ታደሰ
admin@hebrezema.info
1