1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
ጋምቤላ መስከረም 28/2010 በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ በመጡ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው
ለተመለሱና ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የደቡብ ክልል የሦስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የደቡብ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ የሚገኙ ተመላሽ ህጻናት ያሉበትን ሁኔታ
ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ህጻናቱ የተሟላ እንክብካቤ አግኝተው እንዲያድጉ
የተጀመረውን ጥረት ለማገዝ ክልላቸው ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ቀደም ሲል የሙርሌ ታጣቂዎቹ በህዝቡ ላይ በፈጸሙት አሰቃቂ ጭፍጨፋና ህጻናቱ ታፍነው በተወሰዱበት ወቅት የክልሉ
መንግስት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶት እንደነበርና ህጻናቱም ይመለሳሉ የሚል ተስፋ እንዳልነበራቸው ተናግረዋል።

ይሁንና የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን መንግስታት እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባደረጉት ቅንጅታዊ ጥረት ህጻናቱ
ተመልሰው በአካል ለማየት በመቻላቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
admin@hebrezema.info
1
ህጻናቱ የተሟላ ድጋፍና እንክብካቤ አግኝተው እንዲያድጉ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማገዝ የክልሉ መንግስት ሁለንተናዊ
ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ደሴ አረጋግጠዋል።

ህጻናቱ የተሟላ ስብዕና ይዘው እንዲያድጉ ለማስቻል ለተጀመረው ሥራም የደቡብ ክልላዊ መንግስት የሦስት ሚሊዮን ብር
ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት በበኩላቸው፣ የሙርሌ ታጣቂዎች በህዝቡ ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ
በማድረግ ህጻናቶችን አፍነው ቢወስዱም በተደረጉ ጥረቶች አብዛኞቹ ህጻናት ወደአገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን
ተናግረዋል።

ከተመለሱት ህጻናት መካከል ብዙዎቹ ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸው መሆኑን ጠቁመው፣ እነዚህ ሕጻናት የተሟላ ሰብዓዊ
አገልግሎት አግኝተው እንዲያድጉ የክልሉ መንግስት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

ህጻናቱ አድገው ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የክልሉ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ላደረገው ድጋፍና አጋርነት ያላቸውን ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ጊዜያት ከደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ በመጡ የታጠቁ ኃይሎች ከተወሰዱት ከ138 ህጻናት
መካከል የተመለሱት ህጻናት ቁጥር 104 መድረሱን ከክልሉ መስተዳድር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡