1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
ዶ/ር ወርቅነህ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ከሆኑ የአረብ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
May 31, 2018
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወቅነህ ገበየሁ
ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የአረብ ሀገራት አምባሳደሮችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ከአምባሳደሮቹ ጋር በነበራቸው ቆይታም በኢትዮጵያና በአረብ ሀገራት መሀከል ያለው ግንኙነት በተሻለ
ሁኔታ የሚጠነክርበት ጉዳይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም ዶክተር ወርቅነህ ከአረብ ሀገራት አምባሳደሮች ቡድን ሀላፊና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ራሴሽ አል
ሀጅሪ ጋር በፊሊስጤም ጉዳይ ላይ መክረዋል።

ኢትዮጵያ የእስራኤል እና ፊሊስጤም ጉዳይን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ከአፍሪካ ህብረት እና ከተባበሩት
መንግስታት ድርጅት ጋር በቅርበት አንደምትሰራ ዶክተር ወርቅነህ ገልፀውላቸዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በመጨረሻም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ለመላው የእስልምና እምት ተከታዮች መልካም የረመዳን ፆም
ወቅት እንዲሆን መመኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
admin@hebrezema.info
1