1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ አራት ወንዞች ከኢንዱስትሪዎች በሚወጣ
ኬሚካል በከፍተኛ ደረጃ መበከላቸውን አንድ ጥናት አመላከተ።

በጥናቱ በኦሮሚያ የሚገኙት የሃጠበላ፣ ሰበታ እና ሞጆ ወንዞች፤ በአዲስ አበባም የአቃቂ እና ቀበና ወንዞች ለከፍተኛ
ብክለት መዳረጋቸው ተረጋግጧል።

በተያዘው ዓመት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ አፋር ክልሎች እና በአዲስ አበባ በ10 ወንዞች ላይ በሶስት ዙር በተደረገ ጥናት
ነው አራቱ ወንዞቸ በኬሚካል መበከላቸው የተረጋገጠው።

የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር የአካባቢ ብክለት ክትትል ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ዘሪሁን መንገሻ
እንደተናገሩት፥ በወንዞቹ ላይ የኬሚካል ክምችት ተገኝቷል።

ወንዞቹ በእነዚህ ኬሚካሎች የመበከላቸው ምክንያት በአቅራቢያቸው የሚገኙ ፋብሪካዎች የሚለቁት ፍሳሽ መሆኑ
ተነግሯል።

ከፋብሪካዎቹ የሚወጣው እና ወንዞቹን የበከለው ከሜኪካል በሰው እና እንሳሰት ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት የተጠየቁት
ተወካይ ዳይሬክተሩ የጉዳቱን መጠን ለማወቅ የሚያስችል ጥናት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናቶች ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ንጉሴ ስሜ በበኩላቸው፥ በወንዞቹ ውስጥ
የተገኙት ኬሚካሎች ከሰው እና እንስሳት አልፈው ተፈጥሮ ላይ ጉዳት እንደሚደርሱ ጠቁመዋል፡፡

የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ወንዞቹን ለብክለት በዳረጉት የቀለምና የቆዳ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ
እወስዳለሁ ብሏል።

እነዚህ ወንዞች በአቅራቢያቸው ባሉ ኢንዱስትሪዎች ፍሳሽ ምክንያት ለብክለት ተዳርገዋል ሲባል ይህ የመጀመሪያ
አይደለም።

ከአሁን ቀደም ወንዞች መበከላቸው ታውቆ በፋብሪካዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስሰድ ቢጠየቅም፥ እስካሁን ምንም
አይነት እርምጃ ባለመወሰዱ ምክንያት የወንዞቹ የብክለት መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ለወንዞቹ ብክለት መነሻ የሆኑትን ፋብሪካዎች እነማን ናቸው ተብለው የተጠየቁት የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ
ሚኒስቴር የአካባቢ ብክለት ክትትል ዳይሬክተር ተወካዩ አቶ ዘሪሁን የፋብሪካዎችን ስም አሁን አንጠቅስም ነው ያሉት።

ዶክተር ንጉሴ ሚኒስቴሩ በቀረበው ጥናት ላይ ተመስርቶ በፋብሪካዎቹ ላይ እርምጃ ካልወሰደ፥ የወንዞቹ ህልውና አደጋ
ላይ እንደሚወድቅ በሰው እና እንስሳት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ሊጨምር እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።

ሚኒስቴሩ ከጥናቱ በመነሳት በፋብሪካዎቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ቢገልፅም የእርምጃውን አይነት እና
የሚወሰድበትን ጊዜ ግን አልጠቀሰም።
admin@hebrezema.info
1