1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
ኖርዌይ ለኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገች
August 16,2017
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱን የውጭ ሃገር የሥራ ሥምሪት በቅርቡ ለማስጀመር
የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የውጭ ሃገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ በሚሆንበት አግባብ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ የሰራተኛና
ማህበራዊ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ያዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት፥ አዲሱን
የስራ ስምሪት ስራ ላይ ለማዋል ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የማስፈጸሚያ ደንብ፣ መመሪያና የህግ ማዕቀፍ ሰነድ ተዘጋጅቶ እንዲጸድቅ ለሚመለከተው አካል
መቅረቡንም አመልክተዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲሱን የስራ ስምሪት የሚመሩ ዋና ዳይሬክተር ጀኔራልና ሁለት ዳይሬክተሮች ተሹመው ወደ
ስራ መግባታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ቀደም ብሎ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ተደራሽ
ለማድረግም የአደረጃጀትና የአቅም ግንባታ ስራ ተከናውኗል ነው ያሉት፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ አያይዘውም በቅድመ ዝግጅት ስራ ወቅት ከመዳረሻ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መፈራረም፣
ለዜጎች ክትትል የሚያደርጉ የሰራተኛ ጉዳይ አታሼዎች መዘጋጀታቸውንም ጠቅሰዋል።

እስካሁን የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈረመባቸውና በቅርቡ አገልግሎቱ በሚጀመርበት ወቅት ለስራ መሰማራት
የሚቻልባቸው ሃገራት ኩዌት፣ ኳታር እና ጆርዳን መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በአዋጅ ቁጥር 923/2008 የወጣው አዲሱ የውጭ ሃገር ሥራ ስምሪት ውጭ ሃገር በመሄድ ለመሥራት ፍላጎት
ያላቸው ዜጎች መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሰርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል
ነው።
admin@hebrezema.info
1