1
States
Investment
Tourism
Sport
Entertainm.
Radio & Tv  
About us
Contact  
Links
Archives  
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከደቡብ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ
July 14-2020
    Home             News          States         Investment   Tourism         Sport          Entertainm.      Radio & Tv     About us        Contact      Links                  Archives
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
1
አዲስ አበባ ሀምሌ 6/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከደቡብ ክልል የፌደራል፣ የክልል እና
የዞን አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሉ  አመራሮች ጋር ትላንት የተወያዩት በክልሉ ሰላም፣ ልማት፣ የአደረጃጀት ጥያቄዎችና በአገር
ግንባታ ዙሪያ ላይ ነው።

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ቀደም ሲል የነበረው የክልሉ አደረጃጀት ችግር የነበረበትና እስከለውጡ
ዋዜማ ድረስ ጥያቄ ይነሳ እንደነበር አንስተዋል።

በተጨማሪም በክልሉ የልማት፣ የፍትሀዊነት እና የእኩልነት ጥያቄዎች ጭምር ይነሱ እንደነበር ነው ያስታወሱት።

የደቡብ ክልል ፖለቲከኞችና የህብረተሰብ ክፍሎች ላለፉት ዓመታት የነበራቸውን የመበልፀግ እና በእኩልነት የመልማት
ፍላጎት እንዲሳካ የተለያዩ አካላት ቢታገሉም የክልሉ አመራሮች ሚና የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።
admin@hebrezema.info
ችግር በዋናነት የአመራሩ ድክመት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የለውጥ አመራር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በክልሉ የተለያዩ ዞኖች በመዘዋወር የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማወቅ
ከየአካባቢው የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።

በተለይም ከክልሉ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ የሰላም አምባሳደሮች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት መካሄዱን ነው
የጠቀሱት።

የተለያዩ አካላትን በማሳተፍም  ጥናት መደረጉን አመልክተዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የክልሉን ሰላም፣ ልማት እና የህዝቦች አንድነት ችግር ውስጥ በሚጥል መልኩ አንዳንድ
ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች እየተስተዋሉ መሆኑን ዶክተር ዐቢይ ተናግረዋል።

ለዚህ ደግሞ በክልሉ በየደረጃው ያለ አመራር እና አክቲቪስቶች የድርሻቸውን እንደሚወስዱ የተናገሩት ጠቅላይ
ሚኒስትሩ፣ ለውጡን ያመጣው ኃይል መልሶ ድሉን መብላት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

በተለይ በአመራር በኩል ያሉ ችግሮችን የብልጽግና ጉዞን የሚመራው መንግስት ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ
መሆኑን ነው የተናገሩት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት በደቡብ ክልል ለተነሱ ጥያቄዎች የመጨረሻ የመፍትሄ
ሀሳብ በውይይት ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።