1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ
April 24, 2018
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን
ሰጥቷል።

የክልሉ መንግስት ካቢኔ ካሳለፍነው እሁድ ጀምሮ እስከ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የክልሉ መስሪያ ቤቶች አመራሮች
አዳዲስ ሹመትና ሽግሽግ ማድረጋቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

አዳዲስ ሹመቶች

1. አቶ ሀምዲ አደን አብዲ- ምክትል ርእሰ መስተዳደርና የጤና ቢሮ ሀላፊ

2. ወይዘሮ ፈርቱን አብዲ ማህዲ- የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ

3. አቶ አህመድ አብዲ- የውሃ ሀብት ቢሮ ሀላፊ

4. አቶ አብዲሀኪም ኢጋል- የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሀላፊ

5. አቶ ሱልጣን መሀመድ ሀሰን- የመስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ሃላፊ

6. ወይዘሮ ማጂዳ መሀመድ- የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ

7. አቶ ኢብራህም አሊ- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ

8. አቶ ባሼ አብዲ እስማኢል- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

9. አቶ ፉኣድ ጃማ ወላቢ- የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

10. አቶ መሀመድ ረቢዕ ሃጂ አብዲቃድር- ገቢዎች ባላስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ

11. አቶ አብዲላሂ መሀመድ ገርቦ- የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ሀላፊ

12. አቶ ሃሩን ዩሱፍ አብዲ- የንግድ፣ ትራንስፖረትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ

13. አቶ አብዲመሀድ መሀመድ አባስ- የእንስሳትና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ሀላፊ

14. አቶ ጀማል ፋረህ ወርሞጌ- የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ

15. አቶ መሀመድ ቢሌ ሀሰን- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሀላፊና የክልሉ ርእሰ መስተዳደር የሚዲያ
ዘርፍ አማካሪ

16. አቶ ረሺድ ጃመእ ሼር- ምክትል ቢሮ ሀላፊ

17. አቶ ሀሰን አደን ሀሰን- ምክትል ቢሮ ሀላፊ

18. አቶ አብዲአሲስ አህመድ ሀቢዬ- የቆረሄይ ዞን አስተዳዳሪ

19. አቶ ሙሁመድ ሀሰን ሱፊ- የጀረር ዞን አስተዳዳሪ

20. አቶ ሀቢብ አደን- ከወረዳ አስተዳደሪነት ወደ ዞን አስተዳዳሪነት የተዘዋወሩ

21. አቶ መሀመድ አሊ- የዳዋ ዞን አስተዳድር ኃላፊ

በነበሩበት የቀጠሉ

1. ወይዘሮ ሱኣድ አህመድ ፋረህ- የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ

2. ወይዘሮ ረህማ መሀሙድ- የሴቶችና ህፃነት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

3. አቶ ኢብራህም አደን መሀድ- ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

4. አቶ አብዲጀማል አህመድ ቆለንቢ- ጠቅላይ አቃቤ ህግና የፍትህ ቢሮ ሀላፊ

5. እንጅነር አሰድ ኡመር- የገጠር መንገዶች ልማት ባለስልጣን ሀላፊ

በተጨማሪም ክልሉን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (የኢሶህዴፓ) አዳዲስ የፓርቲ
አመራር ምደባዎችን አካሂዷል።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ከደር አብዲ ኢስማእል- የኢሶህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሀላፊ

2. አቶ ኡመር መሀመድ- የኢሶህዴፓ ፖለቲካ ጉዳየች ሀላፊ

3. አቶ አህመድ አብዲ- የኢሶህዴፓ የስራ አስፈፃሚ አባል

4. አቶ አብዲሀኪም ኢጋል- የኢሶህዴፓ የስራ አስፈፃሚ አባል

5. አቶ ሱልጣን መሀመድ ሀሰን- የኢሶህዴፓ የስራ አስፈፃሚ አባል

6. አቶ ጀማል ኢስማን ቆረኔ- የኢሶህዴፓ የስራ አስፈፃሚ አባል
admin@hebrezema.info
1