1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2009፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮሚሽን በሙስና ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር
ያዋላቸው 63 የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በመንግስት ላይ የ170 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ
መሆናቸውን ገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12 ተቋማት በስራ ሃላፊነት የተመደቡ 63 የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በሙስና
ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል 36 በአመራርነት ቦታ ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን፥ 20
ባለሙያዎችና 7 የወንጀሉ ተሳታፊዎች ይገኙበታል።

ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው የመረጃ የማሰባሰብ ሂደት ስድስት
ወራት እንደፈጀበት ገልጿል።

ከፅዳትና ውበት አስተዳደር ኤጀንሲ 29 አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 53 ሚሊየን የመንግስት
ሃብት ምዝብራ በመፈፀም ተጠርጥረዋል።

ከደራሽ ለመርካቶ የሸማቾች ማህበር ሊቀመንበሩን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ጉዳት
ማድረሳቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ከጉሌሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ፅህፈት ቤት አስተዳደር በቁጥጥር ስር የዋሉ 6 አመራሮችና ባለሙያዎች የመንግስት
መሬትን ከህግ ውጪ ለግለሰቦች በመስጠት መንግስትን 600 ሺህ ብር አሳጥተዋል ተብለው ተጠርጥረዋል።

ከቤቶች ልማት ፅህፈት ቤት አራዳ ቅርንጫፍ አንድ የስራ ሃላፊ ከ880 በላይ የሲሚንቶ ከረጢትን ለግል ጥቅማቸው
በማዋል ተጠርጥረዋል።

ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቤቶችና ኮንስትራክሽን ፅህፈት ቤት ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላችውን
የጠቀሰው ፖሊስ የአገልግሎት ፈላጊ መብትን በጥቅም ተደልለው ለማይገባው በመስጠት ውንጀል ነው የተጠረጠሩት።

ጉለሌ ክፍለ ከተማ 7 የስራ ሀላፊዎች ለአምስት ግለሰቦች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚያወጡ ባለ ሶስት መኝታ ኮንዶሚኒየም
ቤቶችን ከህግ ውጭ እንዲያገኙ ማድረጋቸውም ተነስቷል።

ከአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግልት ድርጅት 6 ግለሰቦች በመንግስት ላይ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ
መጠርጠራቸው ነው በመግለጫው የተመለከተው።

ከጉለሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ይዞታ አስተዳደር የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሀሰተኛ ሰነድን ለባንኮች በመፃፍ በቁጥጥር
ስር የዋሉ ሲሆን፥ የአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ አራት የስራ ሃላፊዎችና የወንጀል ተባባሪ
ግለሰብ 4 ሚሊየን የህዝብ ሃብት በመመዝበር መጠርጠራቸው ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ እንድተናገሩት፥ በሌሎች የከተማ አስተዳደሩ
ስድስት ተቋማት በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ተጠርጣሪዎቹ አድርስውታል ከተባለው አጠቃላይ 170 ሚሊየን ብር ውስጥ 24 ሚሊየን ያህሉ በሀሰተኛ የባንክ ሰነድ
የተጭበረበረ መሆኑም ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ድረስ 699 የሙስና ጥቆማዎችን ተቀብሎ የማጣራት ስራ እያከናወነ ሲሆን፥ በቀጣይም በቁጥጥር
ስር የሚውሉ ግለሰቦች ይኖራሉ ተብሏል።በንብረቴ ተሆነ
admin@hebrezema.info
1