1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
ለከተማ ልማት ተብለው የሚነሱ ሰዎችን በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም የሚያስችል ስትራቴጅ ተዘጋጀ
June 27,2018
admin@hebrezema.info
1
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2010 (ኤፍቢሲ) ለከተማ ልማት ተብለው የሚነሱ ሰዎችን በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም
የሚያስችል ስትራቴጅ መዘጋጀቱን የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር አባይ ከፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ስትራቴጀው
ለልማት የሚነሱ ሰዎችን ቅሬታ የሚፈታ ነው ብለዋል።

ስትራቴጂው ክልሎች ለልማት ተነሺዎች ተለዋጭ መሬት ከማዘጋጀት ባለፈ ተነሺዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ቢዝነሶች እና
የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚያቋቁሙበትን አማራጮችንም መያዙን አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል።አዲስ የተዘጋጀው ስትራቴጂ የከተማ ማስፋፋት እና መልሶ ማልማት ስትራቴጅ የሚል ስያሜ የተሰጠው መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስትሩ እንዳሉን የሰዎችን ቅሬታ መነሻ ያደረገው እና ብዙ መፍትሔዎቸን ይዞ ይመጣል የተባለው ስትራቴጂ በመልሶ
ማልማት የሚነሱ አርሶ አደሮችም ይሁኑ የከተማ ነዋሪዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን አማራጮች ክልሎች ያቀርባሉ ተብሏል።

አዲሱ ስትራቴጅ ለልማት ተነሺዎች ብቻም ሳይሆን የተቋሙን ተልዕኮም ለማሳካት ትልቅ መፍትሄን የያዘ ነው ተብሏል።

ስትራቴጅው ተግባራዊ ሲሆን ከተሞችን የማልማት ስራውን ቀልጣፋ በማድረግ የከተሜነትን ምጣኔ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል
አቶ ጃንጥራር።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በከተማ ልማት እና ለመልሶ ማልማት ከቀያቸው እንዲለቁ የሚገደዱ ሰዎች ይስተናገዱ የነበረው የካሳ
አከፋፈል አዋጁን በመከተል ነበር ያሉን ሚኒስትሩ የአሁኑ ስትራቴጅ ግን ሲዘጋጅም ሌሎች ተቋማትን ያሳተፈና የልማት
ተነሺዎች መልሰው መቋቋማቸውን ማረጋገጥ እና ማሳየት አስገዳጅ መሆኑ የተቀመጠበት ነው ብለዋል።

ስትራቴጂው የቅሬታ ምንጮችን የሚፈታ በመሆኑም በፍጥነት እንዲፀድቅ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ስትራቴጅው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ ወደ ተግባር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።