1
    HEBREZEMA.INFO
    INDEPENDENT NEWS & MEDIA
    DESIGNED BY ZEWDU TEKLU
    © COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED 2007.
admin@hebrezema.info
የውዝግቡ መቋጫ ምን ይሆን?
January 14, 2017
የአሜሪካ ምርጫን አሸንፈው ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ከእሳቸው አወዛጋቢነት ባሻገር የምርጫ ሂደታቸውም
እስካሁን ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል። የምረጡኝ ቅስቀሳ ማሰማት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን እልባት ያልተገኘለት የምርጫው
ውዝግብ ሰሞኑን ደግሞ ይበልጥ ተካርሮ የአሜሪካና የሩሲያን ዱላ ቀረሽ ውዝግብ አስከትሏል። ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ካለማንም
ከልካይ ለመግባት ሰባት ቀናትን እየተጠባበቁ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች ለዴሞክራቷ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተን
ሽንፈትና ለእሳቸው ማሸነፍ የሩሲያ ስውር ጣልቃ ገብነት አለበት፤ የዕጩዋን ኢሜይል ብርበራ ከማድረግና አላስፈላጊ ወሬዎችን ከመንዛት
ጀምሮ ለዶናልድ ትራምፕ ስኬት ሩሲያ እጇ እንዳለበት ይፋ አድርገዋል። ሆኖም ዶናልድ ትራምፕ መረጃው ሀሰት መሆኑንና ሩሲያ በጉዳዩ
ላይ እጇ እንደሌለ ቢያስረዱም፤ ከአንድ ግለሰብና ለአሜሪካ ህዝብ ደህንነት ከሚሠሩ ድርጅቶች የቱ በልጦ ነው? የሚለው የስለላ
ድርጅቶቹ አቋም ሩስያ በጉዳዩ ላይ ያላትን አቋም እንድትገልጽ ምክንያት ሆኗል።

ትናንት ቢቢስ ባስነበበው መረጃ፤ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አፈቀላጤ ዲሜትሪ ፔስኮቭ የሩሲያ የስለላ ድርጅት በዶናልድ
ትራምፕ ምርጫ በምንም መልኩ ጣልቃ ያልገባበትና የዴሞክራቲክ ፓርቲን ሽንፈት ለማጎናፀፍ የኢሜይል መረጃቸውን እንዳልፈተሸ
አመልክተዋል። ይልቁንም መረጃ ያልቀረበበት የፈጠራው ወሬ የሁለቱን አገር ግንኙነት የሚያሻክር ነው ሲሉም ኮንነውታል። ዶናልድ
ትራምፕ የዴሞክራት እጩዋን ሂላሪ ክሊንተንን እንዲያሸንፉ ሩሲያ ስውር በሆነ መልኩ ጣልቃ በመግባትና ሴተኛ አዳሪዎችን በማስተባበር
እገዛ አድርጋለች የሚባለውም ከእውነታ የራቀ ነው ብለውታል።

ሚካኤል ኮህን የተባሉት የዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ባለፈው ነሐሴ ወይም መስከረም ወር ወደ ፕራግ ተጉዘው ከክሬምሊን ተወካዮች ጋር
በሚስጥር ተገናኝተው በኢሜይል ብርበራ ላይ ተወያይተዋል በሚል የቀረበባቸውን ውንጀላ እኔ በህይወቴ ወደ ፕራግ ተጉዤ አላውቅም
በማለት ምላሽ ቢሰጡም የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የቪዲዮ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ደግሞ፤ የአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች ይፋ ያደረጉት መረጃ ሆን ተብሎ እርሳቸውን ጥላሸት
ለመቀባትና በሥራቸው ላይ እንቅፋት ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በችካጎ ባደረጉት የስንብት
ንግግራቸው፤ ከስምንት ዓመት በፊት ወደ ሥልጣን ሲመጡ «በምንም መልኩ አሜሪካ የተሻለችና ጠንካራ አገር ነች» ያሉት ፕሬዝዳንት
ኦባማ፤ ዴሞክራሲን በዋስትና የተቀበልነው ስርዓት ባለመሆኑ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ይችላል። በመሆኑም ሁሉም አሜሪካውያን ነገሮችን
በጥልቀትና በተገቢው ሁኔታ በመመልከት ትኩረት መስጠትና ማድመጥ ያስፈልጋል በማለት ሥጋታቸውን አስረድተዋል። አሜሪካውያን
ለዴሞክራሲያቸው ዘብ እንዲቆሙም አስጠንቅቀዋል።

የአገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዝዳንት የሆኑት ኦባማ ለውጥና ተስፋ በሚለው መርሃቸው መመረጣቸው ባይዘነጋም እሳቸውን የተኩ
ዶናልድ ትራምፕ የተሻሉ ፖሊሲዎችን ለመተግበር ቃል ገብተዋል በማለት ቢቢሲ አትቷል። ተጨማሪ አራት ዓመታትን ብቆይ በተደሰትኩ
ነበር። በሕገ መንግሥቱ መሰረት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሊቆይ የሚችለው ሁለት ዙር ብቻ በመሆኑ ለመሰናበት ተገድጃለሁ በማለት ፈገግታ
በተሞላበት ሁኔታ ተሰናብተዋል። ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግሩ የአሜሪካን የዴሞክራሲ ባህል አመላካች ነው ሆኖም የአሜሪካን ዴሞክራሲ
ሦስት ነገሮች ማለትም የኢኮኖሚ ልዩነቶች፣ የዘር ክፍፍሉና በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱ መረጃዎች እየተፈታተኑት ነው ብለዋል።

የአየር ንበረት ለውጥን ለመከላከልና በሙስሊም አሜሪካውያን ላይ የሚፈፀመውን አድሎ እንደሚቃወሙና የትራምፕን አላግባብ የሚባሉ
ንግግሮችን ወርፈዋል። ለውጥ ሊመጣ የሚችለው ሁሉም ዜጋ ሲሳተፍበት መሆኑንም 18ሺ ሰዎች በተሳተፉበት የስንብት ንግግራቸው
አመልክተዋል። ̎ የሆነው ሆኖ የአሜሪካን ህዝብ እንዲያምነኝ የምጠይቀው ነገር ቢኖር ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በራሱ በህዝቡ እንጂ
በእኔ ችሎታ አይደለም፤ ቢሆንም ባገለገልኩባቸው ስምንት ዓመታት ውስጥ ከኩባ ጋር የከፈትነው አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ፣ የኢራንን
የኒኩለር ፕሮግራም ማስቆም መቻላችን፣ የጋብቻ እኩልነትና የ20 ሚሊዮን ዜጎችን የጤና መድህን መስጠት መቻላችን ውጤቶቸችን
የሚለኩባቸው ናቸው ̎ ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።


addiszemen
1